ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Relationship - ግንኙነት. | 1 guest | 2 bots
Pages: 1
Posted on 07-04-17, 01:11 am


Karma: 90
Posts: 456/887
Since: 02-29-16

Last post: 132 days
Last view: 132 days
በፍቅር ህይዎት ውስጥ የሚስተዋሉ አላስፈላጊ ልማዶች
ከስህተት በጸዳ መልኩ ፍጹማዊነት የሰፈነበት የፍቅር ግንኙነት ባይኖርም በጥንዶቹ መካካል የሚኖረው መግባባት ለአብሮነት ቆይታው የራሱ አስተዋጽኦ አለው።
በፍቅር አለም ውስጥ የሚደረጉና የሚስተዋሉ ልማዶች ፍቅርን ለማጠንከርም ሆነ በጊዜ ለመቋጨት አቅም አላቸው።
ከዚህ በታች የተጠቀሱት በፍቅር ውስጥ የሚስተዋሉና ለፍቅር ግንኙነት መቋረጥ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ልማዶች ናቸው።
ሳይናገሩ በሃሳብዎ መወሰን፦ አንዳንድ ጊዜ ቃል ሳይተነፍሱ ያሰቡትን ነገር ልክ በማድረግ እንዲህ ብየ ነበር ማለት በተደጋጋሚ የሚስተዋል መሆኑን ባለሙያዎች ያነሳሉ።
ይህን ማድረግዎ የፍቅር አጋርን የማስቆጣትም ሆነ የማስከፋት አቅም አለው፤ እርስዎ አሰቡ እንጅ ለአጋርዎ አልተናገሩም።
አጋርዎም ቢሆን እርስዎ ያሰቡትን ነገር መረዳትና መተንበይ የሚችልበት አጋጣሚ አይኖርም።
ይህ አይነቱ አካሄድ የአንድ ወገን ውሳኔና ሃሳብ ስለሚሆን የበዛ የሃሳብ ልዩነት ያመጣል።
ስለዚህም ሳይናገሩ ከመደምደምዎ በፊት የሚያስቡትን ነገር በግልጽ መናገርና ማስረዳት መቻልን ይልመዱ።
ቀናተኛ መሆን፦ በፍቅር አለም ውስጥ ቀናተኛ መሆንን አምኖ መቀበልና ጤናማ እንደሆነ ማሰብ የተለመደ ነው።
ካልቀና/ካልቀናች አይወደኝም/አትወደኝም በማለት ቀናተኛ መሆንን የፍቅር ልክ ማሳያና መገለጫ አድርጎ የመውሰድ አዝማሚያውም የበዛና የተለመደ ነው።
ይህ ግን በጥንዶች መካከል አለመተማመንን የሚያሰፋና ጤናማ የፍቅር ግንኙነትን የሚጎዳ ልማድ ነው።
ከዚህ ባለፈ ቅናቱ የአጋርን መገልገያዎች በሚስጥር እስከመፈተሽና እስከመበርበር የሚደርስ ከሆነ ደግሞ ግንኙነትን እስከወዲያኛው የመቋጨት አቅም አለው።
ይህ ለአጋርዎ ክብር አለመስጠት፣ ሚስጥራቸውን ያለአግባብ ለመጋራት መሞከርና አለማመን ነውና በዚያ መልኩ ባይሆን ይመረጣል።
ወቀሳ፦ እርስዎ የሆነ ነገር ማድረግ ፈልገውና አጋርዎ ከዚያ በተቃራኒው ፕሮግራም ኖሮት/ኖሯት ያሰቡት ሳይፈጸም ሲቀር፥ ያንን እያነሱ እንደ ራስ ወዳድ አድርጎ መሳልና መውቀስ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ የተለመደው ነገር ነው።
እርስዎ ከአጋርዎ ጋር ማታ ላይ ወጣ ብለው እራት እየበሉ መጫዎት ፈልገው አጋርዎ በተቃራኒው ሌላ ፕሮግራም ቢይዝ/ ብትይዝ ለምን ከእኔ ጋር ብቻ አልሆነም ብሎ መውቀስና እርስዎን እንደማይሰሙም ሊያስቡ ይችላሉ።
በዚህ ጊዜ ለእርሰዎ ግድ የለሽና የማይጠነቀቅ/ የማትጠነቀቅ እንደሆኑ በመንገር ምናልባት የቃላት ጥቃት ይሰነዝራሉ፤ ይህ ግን ፍጹም አግባነት የሌለውና ስህተት መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በዚህ ጊዜ ፍጹም ራስ ወዳድ እንደሆኑ ማወቅ ይኖርብዎታል፥ ምክንያቱም የተናገሩት እውነታውን ሳይሆን ያሰቡትን ነውና።
ይህን ማለትና ማድረግዎም አጋርዎ ከእርስዎ ሃሳብ ውጭ ሌላ ፕሮግራምም ሆነ ስራ እንዳይሰራ/እንዳትሰራ የማስገደድ ያክል ነው።
ያሰቡት የእራት ሰዓት የአብሮነት ቆይታ እርስዎ በተረዱት መንገድ ሳይሆን ምናልባት አጋርዎ ከወዳጅ ዘመድ አልያም የቅርብ ጓደኛ ጋር መዝናናትና የራሱ/የራሷ ጊዜ እንዲኖር ከመፈለግ አንጻርም ይሆናል።
እናም “አጋዥ የፍቅር አጋር” እና “በግድ ታዛዥ የፍቅር አጋር” የሚለውን በመለየት ግንኙነትን ማጣፈጥና በዚያው ልክም ነገሮችን ይበልጥ ግልጽ በማድረግ ቆይታዎን ያዝልቁ።
ያለፉ ስህተቶችን መጥቀስ፦ በጥንዶች ዘንድ አለመግባባት እና መጠነኛ ቅራኔ ሲፈጠር መሰል ነገሮች ይከሰታሉ።
ከዚህ በፊት በሁለታችሁ መሃል በተፈጠረ አለመግባባት የተከሰቱ አጋጣሚዎችን እያነሱ ማስታወስና ይህን አድርገሃል/አድርገሻል ማለቱ መተራረሚያ ከመሆን ይልቅ መቃቃርን ይፈጥራል።በዚያው ልክም የቆየን መጥፎ አጋጣሚም ያስታውሳልና ያለፈን መጥፎ አጋጣሚ እያነሱ ከመወቃቀስ መታረም ያስፈልጋል።
ሆነዋል ያሏቸውን ነገሮች ነጣጥሎ ማየትና ከፍቅር ህይዎትዎ ጋር አለማስተሳሰርም መልካም ነው።
በፍቅር አለም ውስጥ እስካሉ ድረስም አጋርዎን በሁለ ነገሩ ሊቀበሉት ይገባል።
ከዚህ ባለፈ ግን ሁሉንም አጋጣሚዎች ከፍቅር ህይዎትዎና ከፍቅር አጋርዎ ጋር ማስተሳሰርና ደረሰበኝ ከሚሉት ነገር ጋር የሚያዛምዱት ከሆነም ጥፋት ነው።
ምንጊዜም ቢሆን በእርስዎ በኩል የሆነን ነገር ከፍቅር ህይዎትዎና ከፍቅር አጋርዎ ጋር ማገጣጠሙ ስህተቱ ይበዛልና ነገሮችን ነጣጥለው ለመመልከት ይሞክሩ።
Posted on 07-04-17, 11:54 am


Karma: 100
Posts: 199/625
Since: 08-27-16

Last post: 86 days
Last view: 1 hour
Copied from google

Pages: 1