ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Football / Soccer. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-01-17, 05:46 pm (rev. 1 by ጮሌው on 07-01-17, 05:47 pm)


Karma: 100
Posts: 174/755
Since: 03-20-17

Last post: 17 days
Last view: 17 days
በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የደቡብ አፍሪካውን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ በሜዳው ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል አልቀናውም።ሰንዳውንስ በ85ኛው ደቂቃ አንቶኒ ላፎር ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ነው ያሸነፈው። በመጀመሪያው አጋማሽ መገባደጃ የሳንዳውንስ ተከላካይ ኳስ በእጁ በመንካቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፍፁም ቅጣት ምት ቢሰጥም ሳላሃዲን ሰይድ አምክኗታል።

የቶታል ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ አምስተኛ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት በተደረጉ ሁለት ግጥሚያዎች ሲጀመሩ በኦምዱሩማን ደርቢ የከተማ ተቀናቃኙን አል ሂላልን ያስተናገደው ኤል ሜሪክ 2 ለ 1 አሸንፏል።ድሉን ተከትሎ ሜሪክ ወደ ሩብ ፍፃሜ ለመግባት መንገዱን ሲመቻች ምን ጨዋታ ማሸነፍ ያልቻለው አል ሂላል አጣብቂኝ ወስጥ ገብቷል፡፡ምድብ 1 አሁንም ኤትዋል ደ ሳህል በ8 ነጥብ ሲመራ ሜሪክ በ7 ይከተላል፡፡በቱኒዚያዋ ሴፋክስ ከተማ አል አሃሊ ትሪፖሊ ዩኤስኤም አልጀርን አስተናግዶ 1 ለ 1 ተለያይቷል፡፡

ጨዋታው ኢትዮጵያዊያኖቹ ዳኞች ባምላክ ተሰማ፣ ተመስገን ሳሙኤል፣ ክንዴ ሙሴ እና በላይ ታደሰ መርተውታል።ምድብ ሁለትን አሁንም ዩኤስኤም አልጀር እና አል አሃሊ ትሪፖሊ በእኩል 8 ነጥብ ይመራሉ፡፡የአምስት ጊዜ የአፍሪካ ቻምፒዮኑ ዛማሌክ በ5 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል-(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Pages: 1