ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Education - ትምህርት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 06-25-17, 04:01 am


Karma: 90
Posts: 441/887
Since: 02-29-16

Last post: 133 days
Last view: 133 days
በሰዎች መሀከል የሚስተዋል ትምህርትን የመቀበል ልዩነቶች

“Everybody is A genius. But if you judge a fish by its ability to climbing a tree, it will live its whole life believing that it is stupid”
Albert Einstein

አንዳንዱ ለትምህርት ይፈጠርና ትምህርት ቤት ሳይሆን ሌላ ቦታ በመዋል ጭንቅላቱን እንዳባከነ ብኩን እንደሆነ ይሞታል፡፡ሌላው ደግሞ ለትምህርት ሳይሆን ለሌላ ነገር ይፈጠርና ትምህርት ላይ ሙጭጭ እንዳለ የተፈጠረለትን ነገር ሳይሆን እንደባከነ ይችን ምድር ይሰናበታል፡፡

ለምሳሌ በሰፈራችን ውስጥ የምናቃቸው የሚገርም ጭንቅላት ያለቸው ነገር ግን ትምህርት ቤት ዝር ብለው የማውቁ ቢማሩ የት ይደርሱ ነበር የምንላቸው አይነት ሰዎች አጋጥመውን ሊሆን ይችላል በሌላ በኩል ደግሞ 24 ሰአት የሚያጠኑ ከትምህርት ውጪ ህይወት ያለ የማይመስላቸው ነገር ግን የልፋታቸውን ግማሽ እንኳን ውጤታማ የማይሆኑ ሰዎችም እንመለከታለን::

ከላይ ያየናቸው ሁለት ምሳሌዎች የሚያሳዩን ነገር ተፈጥሮአዊ የሆኑ ሰዎችን ከሰዎች የሚለዩይ የትምህርት አቀባበል ልዩነቶች መኖራቸውን ነው፡፡ ትምህርትን ከመቀበል አንጻር ሰዎች፣ ፈጣን አማካኝ እና ዘገምተኛ ተብለው በ 3 ይከፈላሉ ፈጣን የሚባሉት በተፈጥሮ ከፍተኛ የማገናዘብ ችሎታ ተሰጥቷቸው የሚወለዱ ሰዎች ሲሆኑ ትንሽ አንብበው እና አዳምጠው ብዙ መስራት የሚችሉ ናቸው፡፡ ዘገምተኛ የሚባሉት ደግሞ ብዙ ለፍተው እና አዳምጠውም እንኳን ከልፋታቸው በጣም ዝቅ ያለ ውጤት የሚያመጡ አይነት ሰዎች ናቸው፡፡አማካኝ የምንባለው አብዛኞቻችን ስንሆን ከለፋን ከሰራን የልፋታችንን የምናገኝ ሲሆን ካልሰራን ደገሞ ዝቅተኛ ውጤት የምናስመዘግብ አይነት ሰዎች ነን፡፡

ወላጆች የልጆቻችን ትምህርት ውጤት ቀነሰ ብለን ከመደናገጥ ይልቅ ልጆቻችን የትኛው አይነት ምድብ ውስጥ እንዳሉ ልንገነዘብ ይገባናል፡፡ ዘገምተኛ እና ፈጣን የሆኑ ተማሪዎች በራሳቸው የመቀበል አቅም ልክ ሊማሩ ይገባል፡፡ ዘገምተኞቹ በጣም ተደጋጋሚ የሆነ ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ፈጣን ተማሪዎች ደግሞ በየጊዜው አዲስ ነገር እና ፈተና ይፈልጋሉ ጭንቅላታቸውን የሚፈትን ነገር በየጊዜው እስካላላገኙ እና ልክ እንደ አብዛኞቻችን የሚስተናገዱ ከሆነ ከፍተኛ የትምህርት ፍላጎት ማጣት እና የውጤት መቀነስ ያሳያሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አዲስ ነገርን ለማወቅ ባላቸው ጉጉት የተነሳ እራሳቸውን አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ፡፡የልጆችን አቅም መገንዘብ ካልቻልን እና አስፈላጊውን እርዳታ ካላደረግንላቸው ልጆች ፈጣን ወይም ዘገምተኛ በመሆናቸው ብቻ መድረስ ያለባቸው ቦታ ሳይደርሱ የሚቀሩባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ እንደወላጅ ልጆቻችን ፈጣን ሲሆኑም ፍላጎታቸውን እንዴት እናሟላ ዘገምተኛስ ሲሆኑ እንዴት አርገን ወደፊት እናራምዳቸው የሚለው ጉዳይ ሊያሳስበን ይገባል፡፡

ማጠቃለያ ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት የሰዎች ትምህርት የመቀበል ችሎታ በጣም ይለያያል አንዳንድ ሰዎች ከሚገባው በላይ በፍጥነት ትምህርት የመቀበል ችሎታ ይኖራቸውና ከተባሉት በተጨማሪ አዲስ ነገር እንዲጨመርላቸው ይፈልጋሉ ይህ የማይደረግላቸው ከሆነ በአብዛኛው ክፍል ውስጥ ከትምህርት ውጪ የሆነ ነገር ላይ በመሳተፍ ከአስተማሪ ጋር ይጋጫሉ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የነዚህን ልጆች የሚያሟላ እና ልጆቹ ለአገር ጠቃሚ እንዲሆኑ የሚረዳቸው ለነሱ ብቻ የተቋቋመ ተቋም የለም በዚህ የተነሳ ስንተ ተአምር መስራት የሚችሉ ሰዎች እንደ አብዛኞቻችን ሆነው ቀርተዋል በሌላ በኩል ደግሞ መረዳት ያለባቸውን እና በአቅማቸው መማር ለባቸውንም ልጆች በሚገባው መጠን ባለመርዳታችን ቢያነስ ከደረሱበት በላይ ሳይደረሱ ቆመዋል፡፡

ስለዚህ የሚመለከተው አካል ልብ ሊለው የሚገባው ጉዳይ ይመስለናል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ብዙ የተሰጦ አይነጦች አሉ፡፡ ልጆቻችንን እኛ የፈለግነውን ነገር እንዲሆኑ ሳይሆን የተፈጠሩለትን ተሠጦአቸውን እንዲፈልጉ ብናግዛችው እድገታቸውን እና ተወዳዳሪነታቸውን የማፋጠን እድል ይኖረኛል፡፡

Pages: 1