ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 4 guests
Pages: 1
Posted on 06-24-17, 07:40 pm


Karma: 100
Posts: 164/751
Since: 03-20-17

Last post: 2 days
Last view: 2 days
አንድ የህግ ባለሙያ በባቡር እየተጓዘ ሳለ አንድ
በጣም ቆንጆ የሆነች ልጅ መጥታ ፊት ለፊቱ ከሚገኘው ወንበር
ላይ ተቀመጠች።
:
በዚህም የህግ ባለሙያው ደስ አለው። ቀና ብሎ ሲመለከታት
አይን ለአይን ተያዩ ከዛም ፈገግ አለች።
:
አሁን ደግሞ በይበልጥ ደስ አለው። ትንሽ ቆይታ አጠገቡ ሄዳ
ተቀመጠች። በዚህን ጊዜ እጅግ በጣም ደስ አለው።
:
ትንሽ ቆየችና ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ በሹክሹክታ "ያለህን ገንዘብ;
የATM ካርድህን ከነፓስ ዎርዱ እና የሞባይል ቀፎህን አሁኑኑ
ካልሰጠኸኝ ስትጎነትለኝ እንደ ነበረና ፆታዊ ትንኮሳ እንደደረሰብኝ
እዚህ ባቡር ውስጥ ላሉት ሁሉ በመንገር እጮኃለሁ።" አለችው።
የህግ ባለሙያው በቸልተኝነት ቀና ብሎ ተመለከታትና ከቦርሳው
ውስጥ ወረቀትና እስክሪብቶ አውጥቶ እንዲህ ብሎ ፃፈላት
"ይቅርታ መናገርና መስማት የተሳነኝ ነኝ።
:
እባክሽን ማለት የፈለግሽውን ሁሉ እዚህ ወረቀት ላይ ፃፊልኝ።"
ልጅቷም ቀደም ብላ ስትነግረው የነበረውን ሁሉ ጽፋ ሰጠችው።
የህግ ባለሙያው ወረቀቱን ተቀብሏት በጥሩ ሁኔታ አጥፎ ኪሱ
ከከተተው በኋላ ከተቀመጠበት ተነስቶ ጎርነን ባለ ድምጽ ምን
ቢላት ጥሩ ነው "አሁን እንደፈለግሽ መጮህ ትቺያለሽ።"
:
የታሪኩ ምግባር: ሰነድን በአግባቡ መያዝ ምን ግዜም አስፈላጊ
ነው።

Pages: 1