ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Military. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 06-19-17, 10:33 pm


Karma: 90
Posts: 427/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
ከዚህ በታችም የአሜሪካ ጦርን የተመለከቱ አስገራሚ መረጃዎችን ልናካፍላችሁ ወደናል።
1. የአሜሪካ ጦር ከሀገሪቱ የበለጠ እድሜ አለው
አሜሪካውያን የሀገሪቱ ምስረታ ቀን አድርገው የሚያከብሩት (የነፃነት ቀናቸው) ሀምሌ 4 1776 ነው፤ የሀገሪቱ ጦር ግን ከዚህ አንድ አመት ቀደም ብሎ ነው የተመሰረተው።
የአሜሪካ ጦር ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን ብሪታንያን በመርታት 13 የአሜሪካ ቅኝ ግዛቶች የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አካል እንዲሆኑ ከማድረጋቸው በፊት (በ1775) ነበር የሀገሪቱ ጦር የተቋቋመው።
ጆርጅ ዋሽንግተን በአውሮፓውያኑ ሰኔ 15 “የኮንቲኔንታል አርሚ” ዋና አዛዥ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።
2. የአሜሪካ ጦር ከተማ ቢሆን የአሜሪካ 10ኛው ግዙፍ ከተማ መሆን ይችላል
የአሜሪካ ጦር 1 ሚሊየን በግዳጅ እና ተጠባባቂ ወታደሮች ይዟል።
ይህም በርካታ ነዋሪዎች ኳላቸው የአሜሪካ ከተሞች 10ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ ያደርገዋል።
3. ጦሩ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራተኛን በመቅጠርም ሁለተኛ ደረጃን ይዟል
በአሜሪካ በርካታ ሰራተኞችን በመቅጠር ዋልመርት ቀዳሚ ነው። ኩባንያው 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰራ ሲሆን፥ የአሜሪካ ጦርም ከ1 ሚሊየን በላይ በግዳጅ ላይ ያሉ እና ተጠባባቂ ወታደሮችን ይዟል።
በዚህም ጦሩ 523 ሺህ ሰራተኞችን የቀጠረውን ዩም ብራንድስ በማስከተል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
4. ከተራ ወታደር ቀጥሎ የሚሰጠው ማዕረግ “ስፔሻሊስት” የሚሰኝ ሲሆን፥ ማንኛውንም ተግባር ያለነሱ ፈቃድ ማከናወን አይቻልም። በ2015 የጦሩ ሩብ አባላት (264 ሺህ 890) የ“ስፔሻሊስት” ማዕረግ ተሰጥቷቸው ነበር።
5. ጦሩ በየአመቱ 1 ቢሊየን 3 ነጥብ 7 ቢሊየን ሊትር ነዳጅ ይጠቀማል
በ2011 ጦሩ ይፋ ባደረገው መረጃ እያንዳንዱ ወታደር በየቀኑ በአማካይ ከ83 ሊትር በላይ ነዳጅ እንደሚጠቀም አመላክቷል።
ይህም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለእያንዳንዱ ወታደር ካስፈለገው 3 ነጥብ 7 ሊትር ነዳጅ ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ ነው ተብሏል።
የአሜሪካ ጦር እንደ አውሮፓውያኑ በ2008 ከ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ሊትር በላይ ነዳጅ ለተለያዩ የዘመቻ ስራዎች መገዛቱን ጠቁሟል።
6. አብዛኞቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች በወታደርነት አገልግለዋል
አሜሪካን በፕሬዚዳንትነት ካገለገሉት 44 ሰዎች ውስጥ 31ዱ ለሀገራቸው ወታደራዊ ግልጋሎት ሰጥተዋል።
በሀገሪቱ ጦር ማገልገል ፕሬዚዳንት ለመሆን በመስፈርትነት ባይቀመጥም ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን የጀመሩት ተግባር በቀጣዮቹ ፕሬዚዳንቶች እየተለመደ መጥቷል።
ፕሬዚዳንት ቲዮዶር ሩዝቬልት አሜሪካ እና ስፔን በተፋለሙበት የሳን ዩዋን ተራራ ጦርነት ባሳዩት ድንቅ ብቃት የክብር ሜዳልያ መሸለማቸው ይታወሳል።
ጥቃት ከደረሰበት አውሮፕላናቸው በጥበብ አምልጠው ህይወታቸውን ያተረፉት ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽምከፍተኛ ክብር የሚሰጠውን “Distinguished Flying Cross” ሽልማት የተሰጣቸው መሆኑ አይዘነጋም።
7. ጦሩ የያዘው ቦታ ከሃዋይ እና ማሳቹሴት የቆዳ ስፋት የበለጠ ነው
የአሜሪካ ጦር ለአጠቃላይ አገልግሎት መስጫዎች በአሜሪካ ብቻ ከ60 ሺህ በላይ ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ቦታን ይዟል።
ይህም ጦሩን ከሜሪላንድ፣ ሃዋይ፣ ማሳቹሴትስ እና ቬርሞንት የቆዳ ስፋት የበለጠ መሬት መያዙን ያመለክታል።
ጦሩ ከሃዋይ (28 ሺህ 311 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) እና ማሳቹሴትስ (27 ሺህ 363 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) ድምር የቆዳ ስፋት ከ5 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር የበለጠ ቦታን መያዙ ተጠቁሟል።

Posted on 06-20-17, 06:50 pm


Karma: 95
Posts: 516/850
Since: 07-22-15

Last post: 26 days
Last view: 9 days
Wey tor
Posted on 06-20-17, 09:00 pm


Karma: 90
Posts: 428/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
engdi lezi new alem miferachew
Pages: 1