ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Religion. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 06-14-17, 05:58 am


Karma: 100
Posts: 145/760
Since: 03-20-17

Last post: 18 days
Last view: 2 days
ጊዜ የለም በፍጥነት........
እንደምን አረፈዳችሁ ?
ትላንት ማታ አንድ እንግሊዘኛ ፊልም እያየሁ ነበር፡፡ ፊልሙ ላይ አክተሩ የፈረስ ግልቢያ ተወዳዳሪ ነው፡፡ ሁሌም በልምምድም ቦታ በውድድርም ቦታ ፈረሱን ይጋልበዋል ሲጋልበው በደንብ እየመታው ነው የሚጋልበው፡፡ ይህንን የፈረስ ግልቢያ ትእይንት ስመለከት ብሩኬ የፃፋት ምሳሌና የኛ ኑሮ ትዝ አለኝና ፈገግ አልኩ!! መቼም የሚጋለብ ፈረስ ውድድሩን ለማሸነፍ ብሎ አደለም ፈረሱ የሚሮጠው ጋላቢው የሚመታው ዱላ ስለሚያመው ነው፡፡ ጋላቢው ደግሞ ፈረሱን የሚመታው እንዲያመው ሳይሆን ነቃ እያለ ሮጦ እንዲያሸንፍ ነው፡፡
ይህንን ምሳሌ ወደኛ ስናመጣው የፈረስ ግልቢያው ቦታ የምንኖርባት አለም ናት፡፡ ፈረሶቹ እኛ ነን፡፡ ጋላቢው ደግሞ ፈጣሪያችን ነው፡፡ አዎ ሁሉም ጋላቢ የሚጋልብበት ስልት አለው፡፡ ፈጣሪም እኛ በአለም እንድናሸንፍ ሲፈልግ ጋላቢ ነውና ደጋግሞ ይመታናል፡፡ አንዳንዶች ዱላውን ከክፋት የቆጠሩ ውድድሩን ሲያቋርጡ ሌሎች ዱላው ለማሸነፍ መሆኑ የገባቸው ደግሞ ዱላው ሲበረታ የበለጠ ፍጥነት እየጨመሩ ያሸንፋሉ!!
ስለዚህ አንተም አንቺም ይህንን ፅሁፍ የምናነብ በሙሉ በውድድሩ ቦታ ላይ ነንና ከመቼውም በላይ ፍጥነት እንጨምር አሁኑኑ ወደስኬት ጉዞ ይፍጠን የዛሬው ቀን የፍጥነት መጀመሪያ ይሁን በምሬት ውድድሩን ልናቋርጥ ያልን በሙሉ ወደ ውድድሩ እንምጣ አስቡ ሁላችንም በራሳችን ውድድር ቦታ ከራሳችን ጋር ስለምንወዳደር በባነንና በገባን ሰአት ብንሮጥም ዘገየህ አንባልም!!!!
መልካም ቀን!
፠ለሌላው እንዲጠቅም ሼር ያድርጉ፠

Pages: 1