ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing General Healthcare . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 06-04-17, 07:22 pm


Karma: 100
Posts: 240/426
Since: 07-12-15

Last post: 7 days
Last view: 7 days
የሳይነስ/አለርጂ ህመምን ለማስታገስ
ስድስት ነጥቦች
1. በቂ እረፍት ማድረግ፡
እረፍት መውሰድ ሰውነቶ ህመም የመከላከል አቅሙን እንዲጨምርና በፍጥነት እንድናገግም ይረዳል።
2. ፈሳሽ በብዛት መውሰድ፡
ፈሳሽ በብዛት በምንወስድ ጊዜ በሰውነታችን የሚመነጩ እና ሣይነሶቻችንን የሚደፍኑ ወፍራም ፈሳሾች እንዲቀጥኑ ያደርጋል። አልኮልና ካፊን የበዛባቸው መጠጦች ማስወገድ ይኖርብናል። አልኮል መጠጣት በሳይነሶቻችን አካባቢ እብጠት እንዲኖር በማድረግ ህመሙን ያባብሳል።
3. የሞቀ ውሀ ውስጥ የተነከረ ፎጣ በአፍንጫዎ አካባቢ እና በላይኛው ጉንጮቾ ላይ በማድረግ በፊቶ አካባቢ የሚሰማዎትን ህመም ያስታግሱ።
4. አፍንጫዎን በሚገባ ያፅዱ፡
አፍንጫዎን በንፁህ እና ሞቆ በቀዘቀዘ ውሀ በድንብ አድርገው ያፅዱ።
5. በሞቀ ውሃ ይታጠኑ፡
በፎጣ ተሸፍነው የሞቀን ውሃ መታጠን ህመሞን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።
6. ከጭንቅላትዎ ቀና ብለው ይተኙ፡
ይህም በሳይነሶቻችን ውስጥ የሚገኙ ፈሳሾች በቀላሉ እንዲወገዱ እና መታፈን እንዳይኖር ያደርጋል።
ሌሎችም ያንብቡት። በተን በተን አርጉት።

ጤና ለሁሉም!

source - Dr. Honeliat

Pages: 1