ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Health - ጤና. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-26-17, 07:01 am


Karma: 100
Posts: 229/425
Since: 07-12-15

Last post: 99 days
Last view: 99 days
መጥፎ የእግርና የጫማ ጠረንን ለማስወገድ
7 ቀላል ዘዴዎች

በእግር እና በጫማ ውስጥ በሚፈጠር ከፍተኛ ሙቀት እና የእግር ቁስለት፣ ባክቴሪያ፣ ለእግር የማይስማሙ የካልሲ ምርቶች እና ጫማዎችን መጫማት ለዚህ ችግር እንደ መንስኤ ይወሰዳሉ።

በጫማ ጠረን ምክንያት ብዙ ሰዎች ይሰቃያሉ፡፡ የችግሩ ግዝፈት ምን ያህል እንደሆነ የሚገባን ሰዎች ከእኛ አጠገብ መቀመጥ ሲቸገሩ ስናይ ነው፡፡

ታዲያ ይህን ከሰው የሚያቆራርጥ መጥፎ የእግር እና የጫማ ጠረን እንዴት መከላከል እንዳለብዎት ከዚህ በታች ያሉትን መፍትሄዎች ይመልከቱ።

በጣም ቀላል ናቸው፤ በቤት ውስጥ ሊሞክሯቸው ይችላሉ፡፡ አንብበው ሲጨርሱ በጫማ ጠረን ለሚቸገሩ ወዳጆቻችሁ ሼር በማድረግ ውለታ ዋሉላቸው…

መፍትሄዎች ለእግር፤

1. የሻይ ቅጠል - ሁለት ጥቅል የሻይ ቅጠሎችን በሶስት ብርጭቆ ውሃ ማፍላት እና ከፈላ በኋላ በማውጣት፥ ከዛም በግማሽ ባልዲ ውሃ ቀዝቀዝ ማድረግ እና የውሃ ሙቀቱ ለእግር ተመጣጣኝ ከሆነ እግርን ዘፍዝፎ ከ15 እስከ 20 ደቂቃዎች ማቆየት እና ለሳምንት ያህል ይህን መደጋገም።

2. ዝንጅብል - መካከለኛ ቁመት ያለውን ዝንጅብል በመቆራረጥ እና ለ15 ደቂቃዎች ያህል ውሃ በመጨመር ማፍላት፥ ቀጥሎም ፈልቶ የወረደው ዝንጅብል ላይ ተወቀጠ የቡና ዱቄት መጨመር። ከዛም የሁለቱን ውህድ በአግባቡ አማስሎ በመቀላቀል ውስጠኛውን የእግር ክፍል ዘወትር ከመኝታ በፊት ለተከታታይ ሁለት ሳምንት በአግባቡ አዳርሶ ማሸት።

3. ቤኪንግ ሶዳ - አንድ የሾርባ ማንኪያን ቤኪንግ ሶዳ በእጅ ማስታጠቢያ ግማሽ ለብ ያለ ውሃ መቀላቀል እና እግርን እስከ 20 ደቂቃዎች ድረስ መዘፍዘፍና ከዛ አድርቆ መተኛት፤ ይህን ለአንድ ተከታታይ ሳምንት ማድረግ መልካም ነው።

4. ጨው - እግርን ለብ ባለ ጨዋማ ውሃ መዝፍዘፍም ሌላው መፍትሄ ነው፤ አንድ ተኩል የሾርባ ማንኪያ ጨውን በአንድ ጆግ ውሃ በማፍላት ቀዝቀዝ አድርጎ እግርን ለ20 ደቂቃ መዝፈዝፍና ይህንንም ለሁለት ሳምንታት ያህል መሞከር።

5. ዘይት - ከበቆሎ የተዘጋጁ የአሲድ መጠናቸው ዝቅተኛ የሆኑ ዘይት መሰል ፈሳሽ ኬሚካሎችም ለዚህ ችግር መፍትሄ ናቸው፤ እግር ላይ የሚከሰትን አላስፈላጊ እርጥበትና ላበት በማስወገድ ጤናማ ያደርጉታልና።

6. ሽንኩርት - አነስ ያሉ አራት ራስ ሽንኩርቶችን ልጦ በስሱ መጨቅጨቅ፤ ቀጥሎም በደንብ ታጥቦ የፀዳው እግርዎ ላይ በጨርቅ በማድረግ ማሰር እና ከሶስት ሰአታት በኋላ በመፍታት ማናፈስ።

7. አልኮል - እግርን በደንብ ታጥቦ ማፅዳት እና ማደራረቅ ቀጥሎም የተወሰነ አልኮልን ውስጠኛው እግር ላይ በማፍሰስ ማዳረስ እና ማሻሸት በደንብ ሲደርቅም እግርን አናፍሶ ከደቂቃዎች በኋላ ጫማ ማድረግ።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መፍትሄዎች እግርዎን ከማንኛውም የባክቴሪያ እና የፈንገስ ክምችት የመከላከል እና ምናልባት የተፈጠረ መጥፎ ጠረን ካለም ያንን ለማስወገድ የሚረዱ ናቸው። ከላይ እንደገለፅንላችሁ በጫማ ጠረን ለሚቸገሩ ወዳጆቻችሁ ሼር በማድረግ ውለታ ዋሉላቸው…

ሌሎችም ያንብቡት። በተን በተን አርጉት።
ጤና ለሁሉም!
Posted on 05-26-17, 07:18 am


Karma: 95
Posts: 492/845
Since: 07-22-15

Last post: 152 days
Last view: 11 days
Chama ayayazshn wedjeawalew
Pages: 1