ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Government. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-22-17, 07:32 am


Karma: 90
Posts: 391/879
Since: 02-29-16

Last post: 34 days
Last view: 34 days

ሊቀመንበሩ በመጨረሻው ዘመናቸው በሁሉ ነገር ተስፋ የራቃቸው ይመስሉ ነበር፡፡
መንግስቱ ከሀገር የወጡበት ቀን ግንቦት 13 ፤

ከስሜነህ ጌታነህ

ለ16 አመታት ሀገሪቱን የመራው የደርግ አገዛዝ ሊወድቅ በተቃረበበት ሰአት ሊቀመንበር መንግስቱ ላይ የተለየ ስሜት ይነበብ ነበር፡፡ በጦር ሜዳ ውሎ ድል ማግኘት ያቃተው ይህ ስርአት ወደየት እንደሚኬድ ምን እንደሚደረግ መላው ጥፍት ብሎት ነበር፡፡

የጊዜው የሀገሪቱ ርእሰ -ብሄር መንግስቱ ሁሉን የማህበረሰብ ክፍል እያነጋገሩ ‹‹ወደ ጦርግንባር ይዘመት›› ሲሉ ቀጭን ትእዛዝ ሰጡ፡፡ ‹‹እስከመጨረሻው ድረስ ከመታገል ወደኋላ አልልም›› ያሉት ጓድ መንግስቱ የቅርብ ሰዎቻቸውንም እየሰበሰቡ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ ማፈግፈግ የለም አሉ፡፡ ‹‹እንዲያውም መሳሪያ ከወደየት እናገኛለን ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ አትጨነቁ›› ሲሉ መንግስቱ ሰዎቻቸውን አረጋጉ፡፡ ከመሳሪያ አንስቶ እስከሮኬት ድረስ የማቅረብ እቅም አለን ሲሉ መንግስቱ ሀሳቡን ይበልጥ ዝርዝር አደረጉት፡፡

እነ ኢራቅ ያላቸውን የጦር መሳሪያ ከእጃችን እናስገባለን ሲሉ መንግስቱ ተናገሩ፡፡ ህዝቡም ወይም በጊዜው አጠራር ሸንጎውም የሊቀመንበሩን ዲስኩር ጥሞና ሰጥቶ ካደመጠ በኋላ በጭብጨባ የሊቀመንበሩን ሀሳብ ደገፈ፡፡ መቼም ሰው የፍርሀት ነገር ይሁን አሊያ ለምዶበት እንጂ የሚያጨበጭበው ደርግ እንደመንግስት መውደቂያው እየተቃረበ መምጣቱን ብዙዎች ተገንዝበው ነበር፡፡

በዛን ወቅት የነበሩ እንደ አሜሪካ ሬድዮ ያሉ ጣቢያዎች እውነታውን ለህዝቡ ይነግሩ ስለነበር የሀገሬው ነዋሪ የሊቀመንበሩን በስሜት የተሞላ ንግግር አንዳች ሀቅ እንደሌለው ተገንዝቦ ነበር፡፡ጓድ ሊቀመንበር ግን ህዝቡን ለማነሳሳትና በስሜት ለመሙላት የተቻላቸውን አድርገዋል፡፡ ‹‹በእናት ሀገር ቀልድ የለም›› እያሉ ድምጻቸውን ጎላ አድርገው መናገሩን ቀጥለውበት ነበር፡፡

ሊቀመንበሩ በመጨረሻው ዘመናቸው በሁሉ ነገር ተስፋ የራቃቸው ይመስሉ ነበር፡፡ ከሸንጎው አባላት መካከልም ብዙዎቹ የኮሎኔሉ ነገር ጭንቀት ውስጥ አስገብቶአቸው ነበር፡፡ ዶክተር ሀይሉ አርአያ በሸንጎው ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ እናም ለመናገር እድሉ ሲሰጣቸው መንግስቱን እየተቃወሙ አንድ ሀሳብ ለመድረኩ አበረከቱ፡፡ ‹‹በዚህ የሸንጎ ጉባኤ ላይ በነጻነት ሀሳባችንን መግለጽ አለብን›› ሲሉ ዶክተሩ የመንግስቱን አካሄድ እየተቹ ሀሳብ ሰነዘሩ ፡፡ መንግስቱ በዚህ አስተያየት በጣም ተናደዋል፡፡ ዶክተር ሀይሉ ላይ ጥርስ መንከሳቸው አልቀረም፡፡

በግንቦት ወር አጋማሽ ላይ የመንግስቱ የአገዛዝ ዘመን እያበቃ እንደነበር መንግስቱ ራሳቸው በሚገባ ተገንዝበው ነበር፡፡ ሆኖም አልሞት ባይተጋዳይ ሆነው ነበር፡፡ ደግሞ አንድ አባት እጃቸውን አወጡና ሀሳብ መሰንዘር ጀመሩ፡፡ መቼም መንግስቱ የአጼ ቴዎድሮስን ፈለግ ይከተላሉ እንጂ ለእሳት ማግደውን እንደማይሄዱ ተስፋ አደርጋለሁ›› አሉ ፡፡ ወደ ኋላ ምን እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡

ባለስልጣኖቻቸው ይንቀጠቀጡላቸው የነበሩት መንግስቱ አሁን አንገታቸውን መድፋት ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ የእርሳቸው ሀሳብ በሸንጎው ውስጥ ሚዛን መድፋት አቃተው፡፡ ሸንጎው በእርሳቸው ሀሳብ ላይ ልእልና ያዘ፡፡ መንግስቱ ግን አሁንም ጭንቀት ላይ እንደሆኑ ፊታቸውን የተመለከተ ይረዳል፡፡በዛ ቀውጢ ወቅት የኢህአዴግ ሰራዊት ወሳኝ የሚባሉና ወታደራዊ ፋይዳ ያላቸውን አካባቢዎች ተቆጣጥሮ ነበር፡፡

እሁድ ግንቦት 11 1983 ኢህአዴግ ደሴንና ኮምቦልቻን በራሱ ቁጥጥር ስር አደረገ፡፡ ወታደሩ ተስፋ መቁረጡን አሁን ስራዬ ብሎ ተያያዘው፡፡ ከዚህ በኋላ የሊቀመንበር መንግስቱ ነገር እያከተመለት እንደመጣ ታወቀ፡፡ የ6ሰአቱ የሬድዮ ዜና ይጠበቅ ጀመር፡፡

ዳሪዮስ ሙዲም ከመንግስት ምክር ቤት የመጣለትን መግለጫ ያነብ ጀመር፡፡ ‹‹ በልዩ ልዩ ወገኖች ሲደረግ የነበረው ሰላምን የማምጣት ሂደት አለመሳካቱን መግለጫው ላይ ሰፍሮአል፡፡ መንግስቱ ባይወጡ ኖሮ በቀላሉ ሊቆም የማይችል ደም መፋሰስ ይኖር እንደነበር መግለጫው ያትታል፡፡ በቃ ከዚህ በኋላ የሀገሪቱ እጣ ፋንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ማንም መገመት አልቻለም፡፡

ደራሲ ሀይለመለኮት መዋእል መንግስቱ ሀገር ለቀው የወጡ ሰሞን 40 አመቱን አክብሮ ነበር ፡፡ የመንግስቱ ሀገር ለቅቆ መሄድ ፈጽሞ የማይታመን ነበር፡፡ ግን ሆነ፡፡ ሀይለመለኮት ያን ወቅት አሰብ ሲደርገው ዛሬም መገረም ውስጥ ይገባል፡፡መንግስቱ ሀገር ለቀው እንደሄዱ ወዲያው በእግራቸው የተተኩት ጄኔራል ተስፋዬ ገብረኪዳን ነበሩ፡፡

ለ7 ቀናት ያህል የሀገሪቱ ርእሰ ብሄር በመሆን የመሩት እኚህ ሰው ሰላም ዋናው መሰረት መሆኑን ተናገሩ ፡፡ ይህን አስመልክቶ ያደረጉትን ንግግር ዩቲዩብ ላይ General Tesfaye Gebrekidan last speech. በሚል ርእስ ቪድዮውን መመልከት ይችላሉ፡፡ በዚህ ቪድዮ ላይ የመንግስቱ ምስሎች ከዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ከተሰቀሉበት ሲነሱ ይታያል፡፡

ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ በዛን ሰሞን በመዲናይቱ ዘረፋ ተበራክቶ ነበር፡፡ መንግስቱ ግን ኑሮን በዚምባብዌ ማድረጉን መረጡ፡፡ ልቦለዳዊ ቅርጽ ባለው መልኩ ‹‹የቄሳር እንባ›› በሚል ርእስ ድርሰት ያቀረቡት ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው የመንግስቱን ታሪክ በተለይ ከ1978 አንስቶ ያለውን በልዩ የፈጠራ አጻጻፋቸው አቅርበውት ነበር፡፡ይህ መጽሀፍ በ2007 ለንባብ የቀረበ ሲሆን 408 ገጾች ያለውም ነው፡፡ መንግስቱ በግንቦት 13 ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደነበሩ መጽሀፉ በተለይ ከገጽ 404 አንስቶ እስከ 408 ድረስ ጽፎታል፡፡በከፊል እነሆ ›፡፡

‹‹………….. ወይዘሮ ውባንቺና ልጆቻቸው ጓዝ ጥቅለላ ይጣደፋሉ፡፡ አምባሳደር አስራት ወልዴ ደግሞ የእርሳቸውን ዋና ዋና ንብረት ያዘጋጃሉ፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ ጥድፊያውን ያላዩ መስለው አለፉዋቸው፡፡መሬቱን እየቆነጠሩ በዝግታ ነበር የሚራመዱት፡፡ የቀኝ እግራቸውን በቀኝ እጃቸው በያዙት በትረ- መኮንን መታ መታ ያደርጋሉ፡፡ጥቁረ- ገጻቸው ከሰል መስሎአል፡፡ፊታቸውን እንደአባጨጓሬ ከስከስ አድርገውታል፡፡………››
………..————-……..
‹‹……. መኪናዋ ወደ አየር ማረፊያው ግቢ ገባች፡፡ ሆዳቸው ብርዝ ይልባቸዋል፡፡የአየር መንገድ ሰራተኞች ከቅርብም ይሁን ከሩቅ እንዲያፈጡባቸው አልፈለጉም፡፡ ውስጣቸው በተጻራሪ ሀሳቦች ተናጠ፡፡‹‹ … የምሄደው ወደ ኬንያ ነው፡፡ አስቸኳይ ስብሰባ አለብኝ፡፡ …….›› አሉ መንግስቱ ፡፡
Pages: 1