ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Family. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-18-17, 06:21 am


Karma: 90
Posts: 388/879
Since: 02-29-16

Last post: 69 days
Last view: 69 days
ፍቅር በ“እኔ” እና “አንቺ” !
(መላኩ አላምረው )

እኔ፡-
ፍቅር የገለጽሁ መስሎኝ...
........ ቃል እደርታለሁ
ሁል ጊዜ እልሻለሁ !
.
"አንቺ ማለት ለእኔ፡-
ሁሌ ምትናፍቂኝ
ሁሌ የምትርቢኝ…
አንችን ባየሁ ቁጥር
ደስታዬ ሚጨምር
አንችን ባጣሁ ጊዜ
ሚወረኝ ትካዜ
አንቺ አቅፈሽ ስትስሚኝ
ምታለመልሚኝ
ፊትሽ ሲጠቁርብኝ
ቀን ሚጨልምብኝ
የሥጋዬ እረፍቷ
የነፍሴ ገነቷ…….
የመፈጠሬ ዓለም የመገኘቴ ሥር
የመኖሬ ምክንያት የእስትንፋሴ ምሥጢር
የአዕምሮዬ ዕረፍት የዓላማዬ ጽንዓት
የሕይወቴ ድምቀት የፍቅሬ ምልዓት"
.
እያልሁ እልሻለሁ
ፍቅር የገለጽሁ መስሎኝ...
.......... ቃላት አስውባለሁ።
.
አንቺ፡-
እኔ ቃል መርጬ
እኔ ቃል አምጬ
የምገልጽልሽን ይህን ሁሉ ነገር
በተግባር ሰጠሸኝ ቃል ባለመናገር፡፡

አንቺ’ማ እንደኔ የት ታውቂበት ማውራት
ትሰጫለሽ እንጂ ፍቅርን በምልዓት !
.
ከቶም አይነካካሽ አንቺን ቃል ድርደራ
የፍቅር ንግሥት ነሽ የፍቅር ሙሽራ !
.
ድንቅ ፍጥረት እኮ ነሽ አንቺን ማን ሊተካሽ?
በምን ላስደስትሽ ምን ሰጥቼ ላርካሽ…???
.
ደግሞ እኮ አላፍርም…
‹‹እወድሻለሁ›› ስል… እኔን ብሎ አፍቃሪ
ይልቅ ስሚኝና…
በቃ ለእኔ ስትይ ለዘላለም ኑሪ…!!!!!


››››››› …. እናቴ !… ‹‹‹‹
Pages: 1