ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Travel - ጉዞ. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-10-17, 04:53 am


Karma: 90
Posts: 384/753
Since: 02-29-16

Last post: 1 day
Last view: 1 day
ስለሀገራት መረጃ በጥቂቱ እንካችሁ
#1 የአለማችን ትልቆ ሀገር ሩስያ ስትሆን 17.09 ሚሊየን km2 የሆነ የቆዳ ስፋት አላት::
#2 በአለማችን ላይ በርሀማዋ ሀገር ሊቢያ ስትሆን ከአጠቃላይ የቆዳ ስፍቷ 99% የሚሆነው በበርሀማነት የሚፈረጅ ነው::
#3 በአለማችን ላይ ምንም አይነት ወንዝ የሌላት ሀገር ሳውድ አረቢያ ነች::
#4 ለሴቶች የመምረጥ መብትን ቀድማ የሰጠች ሀገር ኒውዝላድ ነች::
#5 አሜሪካ በአለማችን ላይ ብዙ ክርሰቲያኖች የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን ከአጠቃላይ የህዝብ ብዛቷ 245.9 ሚሊየን የሚሆኑት ክርሰቲያኖች ናቸው:
#6 ብዙ የሆነ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ህዝብ ያላት ሀገር ኢንዶኔዢያ ስትሆን ከ209 ሚሊየን በላይ የሚሆነው ህዝቧ ሙስሊሞች ናቸው::
#7 በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የሀይቅ ብዛት ያላት ሀገር ካናዳ ስትሆን ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ሀይቆች ሲኖራት ይህም በአለማችን ላይ ካሉት የሀይቆች ብዛት 60% ይሸፍናል::
#8 በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የግድያ ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ኤል ሳቫዶር ስትሆን በአማካኝ ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 55.5% የሚሆኑት ግድያ ይፈፀምባቸዋል::
#9 በሀገሯ ፓርላማ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሴቶች ቁጥር ያላት ሀገር ሩዋንዳ ስትሆን በፓርላማዋ ካሉት ጠቅላላ መቀመጫዎ ውስጥ 56.3% (50/80) የሚሆነው የተያዘው በሴቶች ነው::
#10 ዴንማርክ በአለማችን ላይ አነስተኛ የሆነ የሙስና ወንጀል የሚፈፀምባት ሀገር ናት::

Pages: 1