ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Movies. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-06-17, 08:39 pm


Karma: 100
Posts: 92/769
Since: 03-20-17

Last post: 375 days
Last view: 375 days
አንዳንድ ግዜ ምናለ ህይወት አማርኛ ፊልም ላይ እንዳለው ቀላል ቢሆን
ብዬ እመኛለሁ፡፡
...
በቃ አለ አይደል የሆነች የሀብታም ልጅ መንገድ ላይ የመኪና ጎማዋ
ተበላሽቶባት ጎማዋን ስለሰራህላት በፍቅርህ ብትወድቅ...
...
በቃ አለ አይደል ተከራይተህ የምትኖርበት ቤት ኮርኒስ ውስጥ አይጥ
ለመግደል ስትገባ የተደበቀ 300ሺ ብር አግኝተህ ከተማውን በአንድ
እግሩ ማቆም ብትችል...
...
በቃ አለ አይደል ኑሮ መሮህ ጎዳና ተዳዳሪ ስትሆን የሆነች የሀብታም
ልጅ ጎዳና ላይ የተኛህበት የአተኛኘት ስታይልህ ተመችቷት በፍቅር
ብትንበረከክልህ...
...
በቃ አለ አይደል ከአንድ ቦዘኔ ቻይናዊ ጓደኛህ ጋር በመሆን የሰፈርህን
ሰው በሙሉ ሰብስበህ መንገድ ልንሰራላችሁ ስለሆነ ብር አዋጡ
ስትላቸው ያለምንም ቅሬታ ያለ የሌለ ገንዘባቸውን አዋጥተው በከረጢት
ቢያስረክቡህ...
...
በቃ አለ አይደል አንተ ተጎሳቁለህ ስትኖር የሆኑ ከውጪ የመጡ
ዲያስፖራዎች የቤትህን በር አንኳኩተው "አባትህ ከመሞቱ በፊት
ያስቀመጠልህን የሀምሳ ሚሊዮን ብር ውርስ ልንሰጥህ ነው የመጣነው"
ምናምን ብለው በደስታ ጮቤ ቢያስረግጡህ...
...
በቃ አለ አይደል አንዳንዴ ምናለ ህይወት እንደ አማርኛ ፊልም አስማት
ቢሆንልኝ ብዬ እመኛለሁ፡፡ እስቲ አሜን በሉ ህይወታችሁን እንደ አማርኛ
ፊልም የተአምር ህይወት ያድርግላችሁ፡፡
#

Pages: 1