ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Technologies & Discoveries . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-06-17, 12:12 am


Karma: 90
Posts: 381/840
Since: 02-29-16

Last post: 32 days
Last view: 32 days
ሳተላይቶች . . . .
በአሁን ሰዓት እየተጠቀምናቸዉ ያሉ ቴክኖሎጂዎች
የሰዉ ልጆች ከሳተላይቶች ጋር ያለዉን ከፍተኛ የሆነ
ጥገኝነት እንዲጨምር አድርገዋል፡፡ በቤታችን
ወስጥ ተቀምጠን የቴሌቭዢን ስርጭቶችን
ስንከታተል ፤ ዓለም አቀፍ ፕሮግራሞች (እንደ
የዓለም እግርኳስ ዋንጫ ኦሊምፒክ የመሳሰሉት)
በቀጥታ ስንመለከት ፤ ሩቅ ሀገር ካሉ ሰዎች ጋር
በስልክ ወይም ኢንተርኔት ስንገናኝ ወይም ዓለም
አቀፍ የስልክ ጥሪዎችን ስናደርግ ፤ የአየር ሁኔታ
ትንበያ በተለይ ከፍተኛ የተፈጥሮ አደጋ ከመምጣቱ
አስቀድሞ እንድንጠነቀቅ ሲያመላክተን ፤ የስፍራ
መጠቆሚ ቴክኖሎጂ ሰዎችን ወይንም ዕቃዎች
የሚገኙበትን ስፍራ ሲያመላክቱን እና ከዚህም
በጨማሪ ኤሮፕሌኖች እርስ በእርስ ሳይጋጩ
በሰማይ ላይ እንዲሄዱ (በአንድ ሰዓት በአንድ ጊዜ
በሰማይ ላይ ቢያንስ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ
ኤሮፕሌንስ ከቦታ ቦታ ይበራሉ) የሚያደርጉ ሲሆን
ይህ ሁሉ የሚሆነዉ ግን ሳተላይቶች የምድርን
ምህዋር ስለሚዞሩ ነዉ፡፡ እስኪ ያለ ሳተላይት አንድ
ዩናይትድ ስቴት ካለ የፌስቡክ ጓደኛችን ጋር ፈጣን
የኤሌክትሮኒክ መልዕክት ግንኙነት ለማድረግ
እናስብ፡፡ እንዲህ ነዉ የሚሆነዉ፡ ከዩናይትድ ስቴት
እናንተ ፈጣን የኤሌክትሮኒክ መልዕክት እያደረጋችሁ
እስካላችሁበት ስፍራ ድረስ ያለምንም መቆራረጥ
የኢንተርኔት ገመድ ግንኙነቱ ሊኖር ይገባል፡፡ ይህ
ካልሆነ ግን ግንኙነቱ ይቋረጣል ታዲያ 21,176
በላይ ኪ.ሜ. የገመድ ዝርጋታ ዉቂያኖስን አቆራርጦ
፣ ቋጥኙን ደርምሶ ፣ በረሃዉን አካልሎ ፣ ከተማዉን
አልፎ ማድረግ የሚቻል ይመስላችኋል? ከተቻለስ
ምን ያህል የሰዉ ኃይልና ጥሪት ሊወጣ እንደሚችል
አስቡት! ከምንም በላይ ደግሞ የሚወስደዉን ጊዜ፡፡ሳተላይቶች ምንድናቸዉ?
1.የተፈጥሮ ሳተላይቶች
የተፈጥሮ ሳተላይቶች ከምንላቸዉ አንዷ ጨረቃ ናት፡፡
ጨረቃ የመሬት ሳተላይት ናት፡፡ ማንኛዉም ኦርቢቱን
ጠብቆ ቋሚ በሆነ ፍጥነት በጸሃይ ዙሪያ የሚዞር
ከሆነ ሳተላይት ብለን እንጠራዋለን፡፡ የምንኖርባት
መሬት በጸሃይ ዙሪያ ስለምትዞር ሳተላይት እንላታን
ሌሎችም ፕላኔቶች ሳተላይቶች ናቸዉ፡፡
2.የሰዉ ሰራሽ ሳተላይቶች
ከተፈጥሮ ሳተላይት ጋር አንድ ዓይነት ጽንሰ ኃሳብ
ይጋራል፡፡ የሰዉ ሰራሽ ሳተላይቶቸ ምህዋራቸዉን
ጠብቀዉ ቋሚ በሆነ ፍትነት ይጓዛሉ፡፡ የሳተላይቶችን
ታሪክ ስናይ ከ57 ዓመት ያልዘለለ ዕድሜ ብቻ ነዉ
ያላቸዉ፡፡ በ1957 በቀድሞዋ ሲቪየት ዩኒየን በአሁኗ
ሩሲያ የመጀመሪያዉን ‘ስፐትኒክ 1’ የተባለችዋን
ሳተላይት ወደ ምድር ምህዋር አስወንጭፋለች፡፡
አስገራሚዉ ነገር ግን በወቅቱ ከአሜሪካ ጋር
ከነበረዉ የፖለቲካ የበላይነት ፍጥጫ ባሻገር
‘ስፐትኒክ 1 ’ ወደ ምህዋር ስትላክ ምንም ዓይነት
ተልዕኮ አልተሰጣትም ነበር ለሶቭየት ዩኒየን
የዓለማችን ኃያሏን ሃገር ለመሆን ከማገዝ ዉጭ፡፡
ብዙም ሳይቆይ አሜሪካ የራሷን ሳተላይት
ልታስወነጭፍ ችላለች፡፡
Dream Big Ethiopian Team
ሳተላይተቶች ምህዋራቸዉን ጠብቀው እንዲሽከረከሩ የሚያደርጋቸዉ ምንድነዉ?
ሳ ተላይተቶች በተወሰነ ፍጥነት ምህዋራቸዉን
ጠብቀው እንዲሽከረከሩ የሚያደርጋቸዉ የመሬት
ስበት ይባላል፡፡ የመሬት ስበት ሳተላይቶችን ወደታች
ሲስባቸዉ እና የራሳቸዉ ቶሎታ ምህዋራቸዉን
እንዲጠብቁ ደርጋቸዋል፡፡ ይሀን ነጥብ በዝርዝር
እንየዉ፡
አንድ አካል ያለዉ ቁስ ነገር በመሬት ምህዋር ላይ
እየዞረ ወይም እየተሸከረከረ ለመቆየት በቂ ፍጥነት
ሊኖረዉ ይገባል፡፡ ሌላዉ በምህዋር ላይ ያለ ቁስ
አካልን ለማስላት v = (GM/R) ½
ይተገበራል፡፡ v የሳተላይቱ ቶሎታ ሲሆን G ቋሚ
የመሬት ስበት M የፕላኔቷ ግዝፈት R ከምድር
ማዕከል ጀምሮ ያለ ርቀት ይሆናል፡፡ ይህን ቀመር
ስንተገብረዉ ለምህዋሩ የሚያስፈልገዉ ቶሎታ ከ
ቁስ አካሉ ከምድር መሃከል ያለዉ ርቀት ሲባዛ በዚያ
ርቀት ወደ ምድር ያለዉ ሽምጠጣ ስኩዌር ሩት ጋር
እኩል ነዉ፡፡ ታዲያ ሳተላይታችንን በክብ ምህዋር
ላይ 500 ኪ.ሜ. ከፍታ ከመሬት በላይ ማስቀመጥ
ብንፈልግከ (የዘርፉ ጠበብት ምሁራን ዝቅተኛ
የመሬት ምህዋር እያሉ የሚጠሩት) ((6.67 x 10-11 * 6.0 x 1024)/(6900000)) ½ ወይም ደግሞ 7615.77 ሜትር በአንድ ሴኮንድ
ፍጥነት ያስፈልገዋል፡፡ አልቲትዩድ እያደገ በሄደ
ቁጥር በምህዋሩ ለመቆየት ዝቅተኛ ቶሎታ
ያስፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ አንድ ሳተላይት ምህዋሩን
ጠብቆ እንዲጓዝ የሁለት ነገሮች ሚዛን ወሳኝ ነዉ
አንደኛዉ በቀጥታ መስመር ላይ የሚጓዝበት ፍጥነት (ቶሎታዉ) ሲሆን ሌላኛዉ ደግሞ በሳተላይቱና
ምህዋር በሚያደርግበት ፕላኔት መካከል ያለ
የመሬት ስበት ግፊት ነዉ፡፡ ምህዋሩ ከፍተኛ(ሩቅ)
በሆነ ቁጥር ዝቅተኛ ቶሎት ይጠይቃል፡፡ ምህዋሩ
ቅርብ በሆነ ቁጥር ሳተላይቱ ወደ መሬት ተመልሶ
ላለመዉደቅ ሲል በፍጥነት ምህዋሩን ይዞረዋል፡፡
በአሁን ሰዓት ከ50 በላይ ሀገራት በተለያየ መልኩ
በሳተላይት ቴክኖሎጂ ላይ ተሳትፈዉ ይገኛሉ፡፡
ከነዚህም መካከል 10 የሚያህሉ ብቻ ናቸዉ
ሳተላይት የማመንጠቂያ ቴክኖሎጂዉ ያላቸዉ
እነሱም፡- አሜሪካ ፣ ሩሲያ ፣ ፈረንሳይ ፣ ጃፓን ፣
ቻይና ፣ ዩኬ ፣ ህንድ ፣ እስራኤል ፣ ኢራን እና ሰሜን
ኮሪያ ናቸዉ፡፡ የመጀመሪያዉ ሳተላይት
ከተመነጠቀበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ
6600 በላይ የሚሆኑ ሳተላይቶች ወደ ስፔስ
ተወንጪፈዋል፡፡ ከነዚህም መሃል 3600 የሚያህሉ
ምህዋራችንን እዞሩ ሲገኙ በስራ ላይ ያሉት ብዛት
ግን ከ1100 አይበልጥም፡፡ በአስገራሚ ሁኔታ 50
በመቶዉ ያህል ሳተላይቶች ንብረትነታቸዉ የአሜሪካ
ነዉ፡፡ አሁን ላይ እየሰሩ ካሉት 1100 ሳተላይቶች
መካከል ደግሞ 500 የሚሆኑት ከመሬት በላይ 500 ኪ.ሜ. ከፍታ (የዘርፉ ጠበብት ምሁራን
ዝቅተኛ የመሬት ምህዋር እያሉ የሚጠሩት) ላይ
ሲገኙ 50 ያህሉ መካከለኛ የመሬት ምህዋር
ከመሬት በላይ 20000 ኪ.ሜ. ከፍታ ራቅ ብለዉ
የሚገኙ ሲሆን የተቀሩት ጂኦ ስቴሽነሪ ምህዋሮች
36000 ኪ.ሜ. ከመሬት ራቅ ብለዉ ይገኛሉ፡፡
ሁሉም ሳተላይቶች እንደየርቀታቸዉ የየራሳቸዉ
ጥቅም አላቸዉ፡፡ ልብ በሉ ሳተላይቶች የሚዞሩት እኛ
የምንኖርባትን ፕላኔት ምድርን ብቻ ሳይሆን
ሌሎችንም ጨረቃን ፣ ቬነስን ፣ ሳተርንን ወዘተ
ፕላኔቶችን የሚዞሩ ሳተላይቶችም አሉ፡፡
Dream Big Ethiopian Team
ሳተላይቶች እንዴት አስፈላጊ ሊሆኑ ቻሉ?
ለዘመናዊ የመጓጓዣ አገልግሎት ፤ ለመረጃ
ልዉዉጥ ፤ የስፍራ መጠቆሚያ ቴክኖሎጂ ፤
ናቭጌሽን (ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ
መንሸራሸሪያ)፤ ለብሔራዊ ደህንነት ፤ ለጥበቃ
ካሜራ ፤ ለደህንነት ጥበቃ ፤ ለአየር ትንበያ ፤
ለወቶአደር ፤ ለሳይንሳዊ ምርምር እጅግ በጣም
ወሳኝ ናቸዉ፡፡
የሳተላይት ዓይነቶችስ ምን ምን ናቸዉ?
1.ለአየር ትንበያ ተብለዉ ብቻ የሚመነጠቁ
ሳተላይቶች
2.ለስፍራ መጠቆሚያ ቴክኖሎጂ ተብለዉ ብቻ
የሚመነጠቁ ሳተላይቶች፡-ከ20 በላይ ሳተላይቶች
በአንድነት ተጋግዘዉ የናቭጌሽን አገልግሎትን
ይሰጣሉ፡፡
3.ለወቶአደር አገልግሎት ብቻ ተብለዉ የሚመነጠቁ
ሳተላይቶች፡- ምድርን የሚመለከቱ የጥበቃ
ሳተላይቶች ለብሄራዊ ደህንነት
አገልግሎት እና መከላከያ ዲፓርትመንት ጥቅም
ላይ ይዉላሉ፡፡ እነዚህ ሳተላይቶች እጅግ በጣም
ሚስጥራዊ ናቸዉ፡፡
4.ለኮሚኒከሽንና ብሮድካስት ተብለዉ የሚመነጠቁ
ሳተላይቶች፡- ምህዋርe ላይ ካሉ 60 በመቶ
ሳተላይቶች ኮሚኒከሽንና ብሮድካስት ሳተላይቶች ናቸዉ፡፡ የቴሌቭዢን
አገልግሎት ፣ የስልክ ጥሪ እና ሌሎች የኮሚኒኬሽን
አገልግሎቶችን ይሰጣሉ፡፡
5.ለምርምር ተብለዉ የሚመነጠቁ ሳተላይቶች፡-
ያለንበትን ምድርን እና ሌሎችን ፕላኔቶችን ጸሀይን
ጨምሮ ኮዋክብቶችንና
አስትሮይዶችን ለማጥናት ያገለግላሉ፡፡ ከእርሻ ጋር
በተያያዘ ሰብል የሚዘራበትን መሬት መጠቆም ፣
ድርቅ ያለበትን ቦታ መጠቆም እንዲሁም
የሰብሎችን ስርጭት ማሳየት የተወሰኑት ናቸዉ፡፡

Pages: 1