ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Nature - ተፈጥሮ. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-06-17, 12:04 am (rev. 1 by Ye Arada Lij on 05-06-17, 12:05 am)


Karma: 90
Posts: 379/879
Since: 02-29-16

Last post: 37 days
Last view: 37 days
ህዋ ከየት ይጀምራል?
ስርአተ-ፀሀያችን ድንበር ይኖረው ይሆን?
ከስርአተ-ፀሀያችን ውጭ የሚገኘው
በይነኮከባዊ ህዋ(Interstellar space)
በውስጡ ምን ይዟል?
=============== ==ከምድራችን ከባቢ አየር ለጥቆ የሚገኝ፣
አለማትን፣ከዋክብትን እና ሌሎች ግዙፍ
አካላትን የያዘ በመጠነ ይዘት የማይወሰነውን
ወና ስፍራ በጥቅሉ ህዋ ብለን እንጠራዋለን።
ህዋ በቅጡ ይሄ ነው የሚባል መጀመሪያ
ባይኖረውም በአለም አቀፉ የህዋ ህግጋት
(Internatio nal space law) መሰረት
በስምምነት የተቀመጠ ምናባዊ መነሻ
መስመር አለው። ይህ የመነሻ መስመር
'ካርማን መስመር'(Karman Line) ተብሎ
ሲጠራ ከባህር ወለል በላይ መቶ
ኪሎሜትሮች ርቆ የሚገኝ ኢነባር
(Imaginary) መስመር ነው።
.
ከዚህ በፊት እንዳየነው ምድራችን ዋና ዋና
የሆኑ አምስት ከባቢ አየራዊ ርብራቦች
አሏች። ከባህር ወለል በላይ ከ6 ኪ.ሜ አንስቶ
እስከ 20 ኪ.ሜ የሚዘልቀውን ከባቢ አየራዊ
ክልል 'ትሮፖስፌር'(Tropos phere)
ብለን እንጠራዋለን። በዚህ ስፍራ ውስጥ ነው
ዳመናዎች የሚፈጠሩት። አውሮፕላኖችም
ቢሆኑ በዚህ ክልል ውስጥ ነው የሚበሩት።
ከ20ኪ.ሜ አንስቶ እስከ 50 ኪ.ሜ
የሚዘልቀው ክልል 'ስትራቶስፌር'(Strat
osphere) ተብሎ ይጠራል። በዚህ ክልል
ውስጥ የኦዞን ንጣፍ ሰፍሮ ይገኛል። ከዚያ
ቀጥሎ እስከ 85 ኪ.ሜ የሚዘልቀው ክልል
ሜሶስፌር(Mesospher e) ብለን
የምንጠራው ነው። በተለምዶ ተወርዋሪ
ከዋክብት(Meteors) የምንላቸው ፍርክስካሽ
አለቶች ከዚህ ከባቢ አየራዊ ክልል ጋር
በሚያደርጉት ከፍተኛ የሆነ ሰበቃ(Friction)
ነው በመቃጠል የሚነዱት። የሚቀጥለው
ከ85 ኪ.ሜ እስከ 690ኪ.ሜ የሚዘልቀው
ክልል 'ቴርሞስፌር'(Thermo sphere)
ይባላል። በዚህ ክልል ውስጥ ነው ካርማን
መስመር የሚገኘው። መንኮራኩሮች ይህን
ከባህር ወለል መቶ ያህል ኪሎሜትሮች ርቆ
የሚገኝ መስመር እንዳለፉ ወደ ህዋ ገቡ
እንላለን። ከፀሀያችን የሚነሱ 'ፕላስማ'
የተሰኙ ፖርቲክሎች በዚህ ክልል ውስጥ
ከሚገኙ የተለያዩ ጋዞች ጋር በሚያደርጉት
ውህደት ነው አውሮራ የሚሰኘው
የህብረቀለማት ነፋስ የሚፈጠረው። አለም
አቀፉ የጠፈር ማእከል(Internatio nal
space station) ምድርን የሚዞራት በዚህ
ከባቢ አየራዊ ክልል ውስጥ ሆኖ ነው። ከዚህ
ክልል ውጭ በላይ እስከ 10ሺህ
ኪሎሜትሮች የሚዘልቀውን የኤግዞስፌር
(Exosphe re) ክልል ብለን እንጠራዋለን።
(የመጀመሪያ ውን ምስል ይመልከቱ)
.
የቫንአለን የጨረራ ቀበቶ(Van Allen
radiation belt)
=============== ==
የቫን አለን የጨረራ ቀበቶ ምድራችንን ከቦ
የሚገኝ እና መሙል ቅንጣጢት(Charged
particles) የያዘ ኢነባር(Imaginary)
ክልል ነው። ይህ ክልል ከባህል ወለል በላይ
ከ1000ኪ.ሜ አንስቶ እስከ 60,000ኪ.ሜ
ድረስ ያካልላል። በዚህ ክልል ውስጥ የሚገኙ
ቅንጣጢት(particles ) የመጡት
በአብዛኛው ከፀሀይ ነፋሳት(solar winds)
ሲሆን የተቀሩት ከኮስማዊ ጨረሮች
(Cosmic rays) እንደመጡ ይታመናል።
.
ኮስማዊ ጨረሮች ምንድናቸው?
.
ኮስማዊ ጨረሮች ከስርአተ-ፀሀያችን ውጭ
በሚገኘው በይነኮከባዊ ህዋ(Interstellar
space) ውስጥ የሚገኙ እና ከፍተኛ ሀይል
ያለው ፕሮቶች እና አተማዊ ኑክለስ(Atomic
nucleus) የያዙ ጨረራዎች ናቸው። በብዙ
ክፍሎች እንዳየነው ክዋክብት በውስጠኛ
አካላቸው የያዙት ሀይድሮጅን ሙሉ ለሙሉ
ወደ ሂልየም ንጥረነገር ሲቀየር ኖቫ/ሱፐርኖቫ
በተሰኘ ግዙፍ ፍንዳታ ውጨኛ አካላቸውን
እንደሚበትኑ አይተናል። በዚህ ፍንዳታ ወቅት
ከፍተኛ መጠን ያለው ኮስማዊ ጨረሮች
ከአዋራ(ኔቡላ) ጋር ወደ ህዋ ይበተናል። ይህ
አንዱ የኮስማዊ ጨረሮች ምንጭ ነው።
ሌላው እንደምንጭነት የሚጠቀሱት ንቁ
ረጨታዊ ኑክለሶች(Active Galactic
Neucleus) ናቸው። ከዚህ ቀደም በነበረው
ክፍል ሱፐር-ማሲቭ ፀሊም ጉድጉዋዶች
ከፍተኛ የሆነ የጨረራ ቡልቅታ(Jets of
radiation) እንደሚያመነጩ አይተናል።
ይህ ቡልቅታ ኮስማዊ ጨረሮች በውስጡ
እንደያዘ ይታመናል።
.
የቫን አለን የራዲዬሽን ቀበቶ ውስጥ የሚገኙ
ፓርቲክሎች በምድራችን መግነጢሳዊ መስክ
(Magnetic field) ተስበው ምድራችንን
ከበው ይገኛሉ። ይህን በምሳሌ ብናየው፡-
የብረት ፍቅፋቂዎችን ደብተር ላይ ብንበትን
እና ከደብተሩ ስር ጠንካራ ማግኔት ብናኖር
የብረት ፍቅፋቂዎቹ ማግኔቱ ወዳለበት ቦታ
ይሰበሰባሉ። ነገር ግን የደብተሩ ወለል ስላል
ከማግኔቱ ጋር እንዳይጣበቁ ያግዳቸዋል። ልክ
እንደዚህ ሁላ ምድራችንም እንደ ግዙፍ
ማግኔት ናት። መሙል ቅንጣጢቱ
(charged particles) በዚህ ማግኔት
ተስበው ምድራችንን ከበው ተቀምጠዋል።
ወደውስጥ እንዳይዘልቁ የምድር ከባቢአየራዊ
ርብራቦች ያግዷቸዋል። እነዚህን ቅንጣጢት
ከምድር ጋር አጠቃሎ የያዘውን ክልል
የምድር ከባቢ መግነጢስ(Magnetosp
here) ብለን እንጠራዋለን። የቫን አለን
የራዲዬሽን ቀበቶ ከምድራችን ውጪ ሌሎች
ፕላኔቶች ላይም ሊገኝ ችሏል።
.
ከዚህ ክልል እየራቅን ስንሄድ ወደ ጥልቅ ህዋ
(Deep space) እየገባን እንሄዳለን።
ፕላኔቶች እና ሳተላይቶቻቸውን፤ ቇጥቆችን
(Astroids) ፣ ኮሜቶችን እያገኘን
እንሄዳለን።
ታዲያ ስርአተ-ፀሀያችን ውስን የሆነ ገደብ
ይኖረው ይሆን?
(ከዚህ በታች ያለውን ፅሁፍ ፅንሰሀሳብ
በደምብ ለመረዳት ከሁለተኛው ምስል ጋር
እያስተያዩ ቢያነቡት ይመረጣል)
.
ከፀሀይ የሚነሱ ሞቃት ነፋሳት የሚገድባቸው
ነገር እስካላገኙ ድረስ ህዋ ውስጥ ይጉዋዛሉ።
እነዚህን ነፋሳት ሊያቆሟቸው የሚችሉት
ከሚጉዋዙበት ፍጥነት በበለጠ እና በተቃራኒ
አቅጣጫ የሚነፍሱ ነፋሳት ብቻ ናቸው።
እነዚህ ነፋሳት 'በይነኮከባዊ
ነፋሳት'(Interstel lar winds) ተብሎ
ይጠራሉ። በይነኮከብ ማለት 'በከዋክብት
መሀል' ማለት ነው። ከስርአተፀሀያችን ውጪ
የሚገኝ የህዋ ሌላኛ ክፍል ነው። በዚህ የህዋ
ክፍል ውስጥ ከላይ ያየናቸው ኮስማዊ
ጨረሮችን ጨምሮ የተለያዩ ጋዞችን በአዮን፣
በሞለኪውል እና በአተም መልክ ከአዋራ ጋር
አጣምሮ ይዟል። እነዚህን ጥርቅሞች
በአጠቃላይ በይነኮከባዊ ሚድየም
(Interstell ar medium[ISM]) ብለን
እንጠራቸዋለን። ይህንን ISM የያዙ
በይነኮከባዊ ነፋሳት በከፍተኛ ፍጥነት ወደ
ስርአተ-ፀሀያችን ይነፍሳሉ። የፀሀያችን ነፋሳት
እና በይነኮከባዊ ነፋሳት የሚገናኙበት ስፍራ
የስርአተ-ፀሀያችን ድንበር ተደርጎ ይወሰዳል።
.
የበይነኮከባዊ ነፋሳት ፍጥነት ከፀሀያችን ነፋሳት
ፍጥነት በእጅጉ የሚልቅ በመሆኑ የፀሀይ
ነፋሳት በበይነኮከባዊ ነፋሳት ይታጠፋሉ።
በምሳሌ እንየው:- የቧንቧ ውሀ እንክፈት እና
ባዶ ሳፋ እንደቅን፤ ውሀው የሳፋውን ወለል
በነካበት ቅፅበት በየአቅጣጫው በፍጥነት
ይጉዋዝና የሳፋው ገፆች ጋር ሲጋጭ ፍጥነቱን
ይቀንሳል። ውሀውን እንደፀሀያችን ነፋሳት
ብናስበው እና የሳፋውን ገፆች እንደ
በይነኮከባዊ ነፋሳት ብናስበው ከዚህ መረዳት
የምንችለው በይነኮከባዊ ነፋሳት እጅግ ፈጣን
እና ጠንካራ በመሆናቸው የፀሀያችንን ነፋሳት
በማጠፍ ያስቀሯቸዋል። ማጠፍ ብቻ ሳይሆን
ልክ እንደ ሳፋው ገፆች ለስርአተ-ፀሀያችን
ድንበር ያበጁለታል። ይህን ስርአተፀሀያችንን
ከቦ የሚገኝ እና ከድንኩዋ ፕላኔት ፕሉቶ
ምህዋር በእጅጉ ርቆ የሚገኝ ኢነባራዊ
ድንበር ሂልዮስፌር(Heliosph ere) ብለን
እንጠራዋለን። የፀሀይ ነፋሳት ወደዚህ ድንበር
እየተጠጉ ሲመጡ ፍጥነታቸው እየቀነሰ ይሄድና
በሊልዮስፌር ውስጥ የራሳቸውን ስፍራ ይዘው
ይቀመጣሉ። ይህን በዝግታ የሚነፍሱ የፀሀይ
ነፋሳት የተከማቹበትን ስፍራ 'ተርሚኔሽን
ሾክ'(Termination shock) ብለን
እንጠራዋለን። 2 ድንበሮችን አየን፤ አንደኛው
መላው ስርአተ-ፀሀያችንን ከቦ የሚገኘው
ሂልዮስፌር የተሰኘው ኢነባር ድንበር ሲሆን
ሁለተኛው ደግሞ በዚህ ክልል ውስጥ ታቅፎ
የሚገኝ እና በዝግታ የሚነፍሱ የፀሀይ ነፋሳት
የሚገኙበት ተርሚኔሽን ሾክ የተሰኘው ድንበር
ነው። የሂልዮስፌር ውጫዊ ሽፋን 'ሂልዮ
ሽፋን'(Helio sheath) ተብሎ ይጠራል።
ለማጣራት ያክል. . .የፕሉቶን ምህዋር
ጨርሰን ስንሄድ መጀመሪያ የሚገጥመን
ተርሚኔሽን ሾክ ነው። ከዚያ አልፈን ስንሄድ
ስርአተፀሀያችንን የከበበው ሂልዮስፌር
ይገኛል። ይህን ክልል ለቀን ስንወጣ ሌላ
'ቦው ሾክ'(Bow shock) የተሰኘ ስፍራ
ይገጥመናል። የበይነኮከባዊ ነፋሳት
ከሂልዮስፌር ጋር በሚያደርጉት ከፍተኛ ሰበቃ
'ክውታ ሞገድ'(Shock wave)
የሚፈጠርበት ስፍራ ነው። ይህን እንደጨረስን
ከስርአተ ፀሀያችን ወጣን ብለን መናገር
እንችላለን።
[ትንሽ ካደናገረዎት ሁለተኛውን ምስል
ሲያጤኑ በደምብ ይረዱታል]
.
የእነዚህ ድንበሮች መኖር እንዴት መታወቅ
ቻለ?
.
የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቁዋም ናሳ
በ1977(በግርጎርዩስ) ውስጥ በተለያየ ወር
ልዩነት ያመጠቃቸው ቮዬጀር1 እና ቮዬጀር2
የተሰኙት አሳሽ መንኮራኩሮች ስለ ፕላኔት
ጁፒተር፤ ሳተርን፤ ዩራኑስ እና ኔፕቱን ስሪት
አጥንተው እንደጨረሱ ሳይንቲስቶች ወደ
በይነኮከባዊ ህዋ ልከዋቸዋል። ከ37 አመታት
የህዋ ውስጥ ጉዞ በሁዋላ በጁላይ 2012
ውስጥ ሴንሰሮቻቸው የፀሀይ ነፋሳት ፍጥነት
ቀንሶ የበይነኮከባዊ ነፋሳት ፍጥነት
እንደጨመረ ማረጋገጥ ችለዋል። በመሆኑም
ስርአተፀሀያችንን ለቀው ወደ በይነኮከባዊ ህዋ
መግባታቸው እርግጥ ሆኗል።
.
ስለ ስርአተፀሀያችን ድንበሮች ያለንን እውቀት
በሙሉ ያስጨበጡን ቮዬጀሮች ናቸው።
መንትያዎቹ አሳሽ መንኮራኩሮች
የሚጉዋዙበት አቅጣጫ የተለያየ ቢሆንም
ሁለቱም ግን ስርአተፀሀያችንን ለቀው
ወጥተዋል። ቮዬጀር2 አሁን ላይ 'ሳጁታርየስ'
ወደተሰኘው ህብረከዋክብት(Consta
llation) አቅጣጫ በሰኮንድ 16ኪ.ሜ
እየገሰገሰች ጉዞዋን ቀጥላለች። በዚህ ፍጥነት
ከቀጠለች ከ 296,000 አመታት በሁዋላ
ወደ የሰማያችን ደማቁዋ ኮከብ 'ሲረስ'
ልትደርስ ትችላለች። ነገር ግን ሁለቱም
መንኮራኩሮች መንቀሳቀሻ ሀይላቸው የሆነው
'ፕሉቶኒየም ተርሞኤሌክትሪክ ጀነሬተር'
የተሰኘ ባትሪያቸው ከ9 አመታት በሁዋላ በ
2025 ሙሉ ለሙሉ ተሟጦ የሚያልቅ
በመሆኑ መረጃቸውን መላክ ያቆማሉ። ይህ
ማለት ግን ጉዟቸውን ያቁዋርጣሉ ማለት
አይደለም። አሁን ላይ ከቮዬጀሮች የተላክ
መልእክት ምድራችን ለመደረስ ከ16 ሰአታት
በላይ ይፈጅበታል። ቮዬጀሮች በየቀኑ ስለ
ጥልቁ ህዋ ያላወቅናቸውን አዳዲስ
ምስጢራት እያሳወቁን ያሉ፤ በየቀኑ ታሪክ
እየሰሩ ያሉ እና በህዋ ውስጥ የሰው ልጆችን
የወከሉ አምባሳደሮች ብንላቸው ማጋነን
አይሆንም።[ምስል 3 የ ቮዬጀሮችን ገፅታ
ያሳያል]

Pages: 1