ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cars. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 04-28-17, 08:53 am


Karma: 90
Posts: 371/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
የሞተር ዘይት መባከንና መፍትሔው
ዘይት የሞተር ደም ነው፤ ሞተር ያለ ዘይት ለሰከንድ ቢሽከረከር ይበላሻል፤ የዘይት ብክለት ሞተር በሚያረጅበት ወቅት ይከሰታል፤ በየጊዜው የጎደለውን መሙላት ከችግር ያድናል፡፡
ከተወሰነ አገልግሎት በኃላ አብዛኛው ሞተር ዘይት ይባክናል፤ በየ 3200 ኪሜ እስከ አንድ ሊትር የዘይት መባከን የተለመደ ነው፡፡
ለዘይት መባከን አይነተኛ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።
1. የዘይት ፍሰት
በአገልግሎት ብዛት ሲልና ካስኬት ይጨማደዳል፣ ይደርቃል በዚህም ዘይት መፍሰስ ይጀምራል፤ የቫልቭና የታይሚንግ ከቨር ካስኬት/ሲል ፍሰት ብዙም ባይሆን መኖሩ በሚፈጠረው ማዠት ይታወቃል፡፡
የዘይት ፐርሸር ስዊችና የዘይት ፊልትሮ መላላት፣ የቴስታታ ጓርኒስዮን እና ዋናው የኮሎ ሲል መበላት የሚያስከትለው ፍሰት ብዙ ነው፡፡
የፖሲቲቭ ክራንክ ኬዝ ቬንቲሌሽን ሲስተም በክራንክ ኬዝ ውስጥ መጠነኛ ኔጋቲቭ ፐሬሸር መጠበቅ አይነተኛ ተግባሩ ነው፤ በየጊዜው ዘይት ባለመለወጡ የሚፈጠረው የዝቃጭ መከማቸት ሲስተሙን ይዘጋዋል፤ በዚህም ሳቢያ የሚፈጠረው ፕሬሸር ሲልና ካሰኬትን ያበላሻል፡፡
በወቅቱ ዘይት መለወጥ ይህን ክስተት ለማስወገድ ይረዳል፡፡
2. የዘይት መቃጠል
የዘይት መቃጠል ቀደም ባሉት ሞተሮች በጭስ ይታወቃል፤ ዘመናዊ ሞተሮች ግን የተገጠመላቸው ካታሊቲክ ኮንቨርተር ይህን ይደብቃል፤ ያም ቢሆን የተቃጠለው ዘይት ካታሊቲክ ኮንቨርተሩን ከጊዜ በኃላ ያበላሻል፡፡
2.1 በፋሻ እና ሲሊንደር ችግር
በፒስተንና ሲሊንደር መሃል የሚገኘው ፋሻ እምቅን የመከላከል ተግባር ያከናውናል፡፡ ፋሻ የሲሊንደርን መበላት ለመከላከል በሚለቀቀው ቀጭን የዘይት ፊልም ላይ ይንቀሳቀሳል፤ ዘይት ከሌለ ወይም የተቃጠለ ዘይት ከተጠቀምን ሲሊንደሩ መንቀሳቀስ ያቅተዋል፡፡
ስለዚህ የዘይቱን ሊቤሎ መጠበቅና ወቅቱን ጠብቆ መለወጥ ያስፈልጋል፡፡የዘይት መለወጫ ጊዜ ሲያልፍ ዘይቱ ይቀጥናል፣ ፋሻ የፒስተን ግሩቭ ላይ ይጣበቃል፤ ዘይት በፋሻው መጠረጉ ይቀርና ወደ ነዳጅ ማቀጣጠያ ቻምበር ገብቶ ይቃጠላል፤ የፒሰተኑ እንቅስቃሴ እጅግ ፈጣን በመሆኑ (ከ 2000 እስከ 4000 ዙር በደቂቃ) በርካታ ዘይት ይባክናል፡፡
የተበላ ወይም ግሩቭ ውስጥ የተጣበቀ ፋሻ መኖሩ የሚታወቀው በኮምፕሬሽን ቴስት ነው፡፡ ፕሬሸሩ አነሰተኛ ሆኖ ጠብታ ዘይት ሲጨመርበት ከ 15 ፒኤስአይ በላይ ጭማሪ ካሳየ ችግሩ አለ ማለት ነው፡፡
አንዳንዴ የኬሚካል ትሪትመንት በመጠቀም የተጣበቀውን ፋሻ ማስለቀቅ ቢቻልም ዘላቂ መፍትሔ አይሆንም፤ የግድ መለወጥ አለበት።
በዚህ ሳቢያ የሚፈጠር ችግርን ናኖ ኢነርጃይዘር በመጠቀም በቀላሉ ማስወገድ ይቻላል።
2.2 የቫልቭ ጋይድ ሲል ችግር
ቫልቭ የሲሊንደሩን መውጫና መግቢያ በመዝጋት የነዳጅ ማቀጣጠያ ቻምበርን የማመቅ ተግባር ያግዛል፤ የቫልቭ ጋይድ ሲል ደግሞ ቫልቩ የሚንቀሳቀስበትን ቱቦ (ጋይድ) ይዘጋል፡፡ ይህ ሲል ከተሰበረ ወይም ከተበላ ዘይት ወደ ቫልቭ ጋይድ ቀጥሎም ወደ ሲሊንደር እንዲገባ ምክንያት ይሆናል፤ የገባው ዘይትም ይቃጠላል፤ ዝቃጭ በቴስታታ መከማቸት ዘይትን ወደ ዘይት ማከማቻ ቋት መላሽ ቱቦን በመዝጋት ችግሩን የከፋ ያደርገዋል፡፡
ቴስታታ ሳይወርድ ቫልቭ ጋይድ ሲል በቀላሉ በመለወጥ ይህን ችግር ማስወገድ ይቻላል፡፡
3. ሌሎች የማይናቁ ችግሮች
አግባብ ባልሆነ ወይም ጥራቱን ያልጠበቀ ወይም
የማይመጥን የአየር ፊልትሮ መጠቀም አቧራ ወደ ሲሊንደር እንዲገባ በማድረግ ፋሻ እንዲጎዳ አልፎም
ዘይት እንዲቆሽሽ ያደርጋል፤ ቆሻሻ ነዳጅ መጠቀምም ተመሳሳይ ችግር ይፈጥራል፡፡ ከተፈቀደው በላይ ወፍራም ዘይት መይም ከቀደመው ዘይት ላይ ሌላ አይነት ዘይት መደባለቅ የዘይትን አይነተኛ እንቅስቃሴ ያውካል።
ስለሆነም ተገቢውን ክትትል ማድረግና የተፈቀደውን ብቻ መጠቀም ይመከራል።
ናኖ ቴክ ኢስት አፍሪካ

Pages: 1