ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Airlines. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 04-25-17, 05:59 pm


Karma: 100
Posts: 209/426
Since: 07-12-15

Last post: 37 days
Last view: 37 days
/ዩጋንዳዊው ጳጳስ ዶ/ር ፍሬድ ሼልደን ምዌሲንግዋ በጉዞ ማስታወሻቸው እንዳሰፈሩት/

አፍሪካዊያን ከሀገራቸው ውጪ ተገናኝተው ወግ ከጀመሩ የወሬያቸው ርእስ ወዲያው በሀገራቸው ላይ የሚያጠነጥን ይሆናል ሲሉ ነው ዩጋንዳዊው ጳጳስ ዶ/ር ፍሬድ ሼልደን ምዌሲንግዋ ወጋቸውን የሚጀምሩት፡፡

በቅርቡ በአዲስ አበባ አሳብረው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ 38 ሰአታት ወደ መኖሪያቸው ካናዳ ሲበሩ ከአፍሪካዊያን ጋር መጓዛቸውን የሚነግሩን ጸሀፊው በጉዞው የገጠማቸውን ያሰፈሩበት መንግድ እጅግ በሳል ሀሳቦችን የሚያነሳ ሆኖ ነው ምናገኘው፡፡

በአውሮፕላን ላይ ስለአፍሪካ ሀገራት ያደረኩት አጭር ግምገማ ሲሉ ወጋቸውን ስም የሰጡት ሲሆን ከኮንጎአዊ፣ ከናይጄሪያዊና ከደቡብ ሱዳናዊ ዜጎች ጋር የተጨዋወቱትን ፍሬ ነገር ከአውሮፕላኑ አስተናጋጆች ስለኢትዮጵያ ጠይቀው ከሰሙት እውነታ ጋር በማነጻጸር ስለአፍሪካ ሀገራት የሚሰማቸውን ምልከታ ይናገራሉ፡፡

ሀገሬ ዩጋንዳ በማንኛውም መመዘኛ የአፍሪካ ሀገራትን ትበልጣለች ሲሉ የሚናገሩት ጸሀፊው ይሁን እንጂ ደረጃ ስጥ ብባል ከእርሷ የማስቀድመው ኢትዮጵያን ነው ይላሉ፡፡ ከዚሁ ወጋቸው በጥቂቱ እንቀንጭብለት፡-

ከዩጋንዳ ኢንቴቤ ወደምኖርባት ካናዳ ቫንኩቨር ስበር እስከ አዲስ አበባ ያለውን መንገድ የተጓዝኩት ከአንድ የኮንጎ ዜጋ ጎን ተቀምጬ ነበር፡፡ ጉዞው ሲጀመር እኛም ወግ ጀመርን የሚሉት ጸሀፊው ኮንጎአዊው ካናዳ ካልጌሪ በቀን ስራ ኑሮን የሚገፋ መሆኑንና ሀገሩ ደርሶ ወደዛ እየተመለሰ መሆኑን ነገረኝ ይላሉ፡፡

ኮንጎአዊው የኔን ሀገር ዩጋንዳን እንደሚወዳት ነገረኝ፤ ዩጋንዳ ከምንም በላይ ልክ እንደቤቱ ሆና እንደምትታየውና አንድ ቀን አነስተኛ ሁዳድ ገዝቶና ጎጆ ቀልሶ በዛ ለመኖር እንደሚያልም አጫወተኝ፡፡ ኮንጎአዊው ሀገሩ በብጥብጥ የተሞላች መሆኗን ቢናገርም ሀገሩ ሲመለስ ግን በርካታ ሰዎች በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥም ሆነው ሀብት ንብረት አፍርተው እንደተመለከተ ይገልጻል፡፡

እኔ ካናዳ ላቤን ጠብ አድርጌ በማገኘው ዶላር ላደርገው የማልችለውን በብጥብጥ ውስጥ ባለችው ሀገሬ ኮንኮ አንዳንዶች ሲከብሩባት አየሁ አለኝ፡፡ ከዚህ ተነስቶም ሀገሬ የተመቸ ስራ ያለኝ መሆኑን ጠየቀኝ የሚሉት ጸሀፊው ዩጋንዳ ጥሩ ስራ ካለኝ በፍጹም በስደት እንዳልኖር መከረኝ በማለት ይተርካሉ፡፡ ካናዳ የምታገኘውን ገቢ መንግስት በታክስ ይወስድብሀል ሲልም ኮንጎአዊው መናገሩን ያስነብቡናል፡፡

አዲስ አበባ ደርሰን አውሮፕላን ስንቀይርና ወደካናዳ ጉዞ ስንጀምር ደግሞ ከአንድ ናይጄሪያዊና ደቡብ ሱዳናዊ ዜጋ መካከል መቀመጫ ደረሰኝ የሚሉት ጸሀፊው ከነዚህ ሰዎች ጋር ያወጉትንም ጨረፍ አርገው ያስነብቡናል፡፡ ደቡብ ሱዳናዊው ስለሀገሩ የሚለው ብዙም ባይኖረውም ናይጄሪያዊው ግን መድረኩን ተቆጣጥሮ ብዙ ሲያወራን ቆየ፡፡ በእንግሊዝ መማሩንና ሰፊ ልምድ መቅሰሙን ሚናገረው ናይጄሪያዊው በመካከለኛ እድሜ ላይ ያለና መረጃዎችን አጣቅሶ የሚናገር ብዙ ያነበበ ሰው ይመስላል፡፡

ባለቤቱን ለማስታመም ወደካናዳ አቅንቶ በዛ 16 አመታት መኖሩን የሚናገረው ናይጄሪያዊው 6 ልጆቹንም በዛ እንደወለደ አጫወተን፡፡ ስለሀገሩ በናፍቆት የሚያወራው ግለሰቡ አንድ ቀን ጡረታ ሲወጣ ናይጄሪያ ጠቅልሎ እንደሚገባ በስሜት አጫወተን፡፡ ይሁን እንጂ ስለሀገሩ ሙስና በተነሳ ጊዜ ሀገሩ በዚህ በኩል ከዩጋንዳ ጋር የሰማይና የምድር ያክል እንደምትራራቅ የነገረንና የሚያውቃቸው ሰዎች ጭምር በሙስና ሀብት እንዳካበቱ ቢናገርም አሁን ላይ ግን መንግስት አዲስ ዘመቻ በመጀመሩ ውጤት መምጣቱን ሊያሳምነን መሞከሩ አልቀረም ይላሉ፡፡

ደቡብ ሱዳናዊው የሚለው ብዙ አልነበረም፡፡ በጦርነትና ብጥብጥ ውስጥ የምትገኘው ሀገሩ ሰላም ይወርድባታል ብሎ ብዙም ተስፋ እንደሌለው ነው የነገረን፡፡ ከካናዳ ካልጌሪ ዩጋንዳ የመጣው በስደት ላይ ያሉ ዘመዶቹን ለመጠየቅ እንደነበር ነው ያወጋን፡፡ ቀደም ብዬ ከኮንጎአዊው ተጓዥ እንደሰማሁት ከሆነ ደቡብ ሱዳን ነጻ ስትሆን የተማሩና በካናዳ ያሉ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ተስፋ ሰንቀው ወደሀገራቸው ተመልሰው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የተመኙት አልሆን በማለቱ ወደመጡበት ተመልሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግስት እና በኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር መካከል የሰላም ስምምነት ተፈረመ
አሁን ላይ በውጪ ሆነውም ዲንካና ኑዌሮች እየተባባሉ ደቡብ ሱዳናዊያን በየጎዳናው ሲጋጩ ማየት የተለመደ ነው ሲል ነበር ኮንጎአዊው ያጫወተኝ፡፡ የደቡብ ሱዳናዊውን በሀገሩ ላይ የሚንጸባረቅ ተስፋ የቆረጠ አስተያየትን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ነበር ያዳመጥኩት በማለትም ጸሀፊው ይተርካሉ፡፡

ዩጋንዳዊው ጸሀፊ ዶ/ር ምዌሲግዋ ትረካቸውን ሲቀጥሉ ስለ እናት አፍሪካዬ ይህን መሰሉን ሁኔታ ስሰማ ዩጋንዳዊ አድርጎ ስለፈጠረኝ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ ይላሉ፡፡ ይህን እያሰላሰልኩ አይምሮዬ ከምበርበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦኢንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን አልፎ ይቀዝፍ ገባ፡፡ አንዲት የበረራ አስተናጋጅ ኢትዮጵያ ከ 50 በላይ አውሮፕላኖች እንዳልዋትና ፈጣን እድገት እያስመዘገበች እንደምትገኝ የነገረችኝን አስታወስኩ፡፡ ኢትዮጵያ ከቅኝ ግዛት ነጻ ሆና የኖረች ሀገር መሆንዋን አስታውሼ ይህ ይሆን እንዴ ሀገሪቱ እንድታድግ ያደረጋት ስል ለራሴ ጠየኩ፡፡

ናይጄሪያዊው ወዳጄ ሀገሩ በነዳጅ ሀብት የበለጸገችና በአፍሪካ በኢኮኖሚዋ ግዙፍ መሆንዋን የነገረኝ ውል አለብኝ፡፡ ሀገሪቱ ይህን ሁሉ ሀብት ይዛ አንዳችም አውሮፕላን ሳይኖራት በአቡጃ አየር ማረፊያ ሜዳ ላይ ግን ከ 200 የማያንሱ የቱጃሮችና የባለስልጣናትን የግል ጀት መቁጠር ይቻላል ሲል ነበር የነገረኝ፡፡ አዎን ልክ እንደናይጄሪያዊው ሁሉ ሁላችንም ስለሀገራችን የየራሳችንን ችግሮች መንቀስ እንችላለን፡፡ ይሁን እንጂ

በዚህ የበረራ ላይ አጭር ግምገማዬ ኢትዮጵያ ከሀገሬ ዩጋንዳ ጭምር የምትበልጥ ሀገር ሆና ነው ያገኘኋት ሲሉ ነው ጸሀፊው በግሩም ትረካቸው ስለአፍሪካችን የሚያስመለክቱን፡፡

Pages: 1