ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing People . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 04-25-17, 01:17 am


Karma: 100
Posts: 81/769
Since: 03-20-17

Last post: 219 days
Last view: 219 days
✍ ውሾች እና ድመቶች አልጋ ላይ እንዲዘሉ እየፈቀድን ድሆች ግን የግቢያችን ድንጋይ ላይ እንዲቀመጡ አንፈቅድም ፡፡
✍ የሰው ዋጋው እየቀነሰ የዶሮ እና የእህል ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ በርትተህ ጸልይ፤ ጤናማ አካሄድ አይደለምና ፡፡✍ የውሻ ቡችላ በዋጋ እየተሸጠ ሰውን ግነ በነጻ የሚፈልገው ሲታጣ ዘመኑ መክፋቱን እወቀው ፡፡
✍ ስለ ብርቅየ እንስሳት ብዙዎች እያለቀሱ ይናገራሉ በምግብ እጥረት ስለሚሞቱት ሕጻናት ግን ቃልአይናገሩም።
✍ ስለ ጠፈር ሳይንስ ብዙ ይወራል (ይሰራል) የምድር ኑሮ ግን ሲተራመስና ሲጎሳቆል ያስተዋለ የለም ፡፡
✍ የወደቁ የታዋቂ ሰዎች ሐውልቶች መልሶ ለመትከል ገንዘብ ይሰበሰባል፤ በየጎዳናው ዳር ስለወደቁት ምስኪን ሕጻናት ግን ምንም አይባልም ፡፡
✍ በዚች ምድር በሚልዮን ብሮች እስርቤቶች ይገነባሉ ሚልዮኖች መጠልያ ሳይኖራቸው፡፡
✍ ስለ አየር መበከል ዓለም በሙሉ ይጮሃል ስለሰው ልጆች ስነ ምግባር መመረዝ ግን ማንም ምንም አይልም፡፡
✍ ሰዎች ሆይ ከዚህ አፍ እና ልብ ከተለያዩበት ትያትረኛ ማንነታችን ፈጥነን እንውጣ ፡፡
☞☞ ሰዎች ሆይ የሚቀድመውን ብናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለን ነበር ፡፡
ምንጭ:- #ከደራሲያን ዓለም
Pages: 1