ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Health - ጤና. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 04-23-17, 09:30 pm (rev. 1 by Ye Arada Lij on 04-27-18, 06:36 am)


Karma: 90
Posts: 368/879
Since: 02-29-16

Last post: 34 days
Last view: 34 days
ልቢቱን ልብ እንበላት፤ የልብ በሽታ ምክንያቶች፣ ምልክቶችና ሕክምና
ልብ ከሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ውስጥ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ እውቅና የተሰጣት አባል አካል ናት ማለት ይቻላል፤ ከ20 ሺህ ዓመታት በፊት በዋሻዎች ውስጥ በሚገኙ ስዕሎች ውስጥ ሳይቀር የልብ ስዕል ይገኛል፤ ጥንታዊያን ግሪኮች ደግሞ የአንድ ሰው ብልህነት በልብ ላይ ይገኛል ብለው ያምኑ ነበር፤ አብዛኞቻችን ደግሞ ልባችንን የነብሳችን ወይም የስሜታችን መገኛ ቦታ አድርገን እናቀርባለን፤ በዕለት ተለት ቋንቋችን ውስጥም መከፋታችንን ለመግለፅ ልቤ ተሰብሯል፤ ማፍቀራችንን ለመግለፅ ደግሞ ልቤ ተማርኳል እንላለን፡፡ ታዲያ ልቢቱን ምን ያክል እናውቃታለን?
ማፍቀራችንን ለመግለፅ ደግሞ ልቤ ተማርኳል እንላለን
የልባችን መጠኗ የእጅ ጭብጣችንን ያክላል፤ የተሰራችው ደግሞ በተወሰነ የግዜ ልዩነት ወይም አንፃረ ጊዜ በሚኮማተርና በሚፍታታ ጡንቻ ሲሆን ደም ከልብ ጨምቃ በመግፋት በመላ ሰውነት እንዲዘዋወር ታደርጋለች፡፡ ልብ ያለማቋረጥ ብትመታም በምቶች መኻከል ግን ለክፍልፋይ ሰኮንዶች አፍታ ጦንቻዎቿ ያርፋሉ፤ ልብ በአንድ ሰው የህይወት ዘመን፣ ለምሳሌ 76 ዓመት የኖረ ሰው ልቢቱ ወደ 2.8 ሚሊየን ጊዜ መትታለች፤ በነኝህ ሁሉ ጊዜያት ደግሞ 169 ሚሊየን ሊትር ደም አዘዋውራለች፡፡ ልብ፣ ደም እና የደም ስሮች በአንድ ላይ የዘውረ ደም ስራን በጋራ ያከናውናሉ፤ የዘውረ ደም ስርዓት ደግሞ ኦክስጅንና ምግበ ንጥረነገሮች ወደ ተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች የሚያጓጉዝ እንዲሁም የተቃጠለ አየርና ሌሎች ውጋጅ ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን እንዲወገድ የሚያደርግ ዘዋሪ ስርዓት ነው፡፡ ስለዚህ ልባችንን ለዘውረ ደም ስርዓት እንደ ዋና አንቀሳቃሽ ኃይል ወይም ጀነሬተር ልንላት እንችላለን፡፡ ልብ እስከ ህይወት ፍፃሜ ያለማቋረጥ መምታት ያለባት አባለ አካል ነት፤ አለበለዚያ አንጎላችን፣ ራሷ ልብ እና ቀሪው የሰውነታችን ክፍሎች በቋሚነት ኦክስጅንና ኃይል ስለሚያስፈልጋቸው ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ ልብ መምታት ካቆመች ሞት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይከተላል፡፡
የሰው ልብ መጠኑ የእጅ ጭብጣችንን ያክላል
የልብ ስራ ደምን ወደተለያዩ የሰውነት ከፍሎች ከማዳረስም በላይ ነው፤ ልብ ሰውነት ለሚፈልገው የኦክስጅን ፍላጎት ፈጣን ምልሽ መስጠት አለበት፤ ልባችን በእንቅልፍ ሰዓት፣ ወይም በከፍተኛ የአካል እንቅስቃሴ ጊዜያትና የአደጋ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ምላሽ የምትሰጥበት መንገድ ይለያያል፡፡ የልብን ድምፅ ሲመታ የምንሰማው ጡንቻዎቹ ሲኮማተሩና ሲፍታቱ ሳይሆን የልብ ክፍልፋዮች ባልቦላ የደም ፍሰትን ለመፍቀድና ለመግታት ሲከፈትና ሲዘጋ ነው፡፡ የሰው ልጅ ልብ አራት ክፍልፋዮች ያሉት ሲሆን እነኝህ ክፍላፋዮች በኦክስጅን የበለፀገ ደም ወደ ተለያየ የሰውነት ክፍል በግፊት የሚያሰራጩና የተቃጠለ አየርና ውጋጅ ቆሻሻዎችን የያዘ ደም ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ለተሃድሶ ወደ ሳንባ እንዲሄድ የሚያስችሉ ክፍሎች ናቸው፡፡ ሁኔታውን ለመረዳት ጥቂት ስለ ዘውረ ደም ስርዓት ማየት ተገቢ ነው፡፡
የዘውረ ደም ስርዓት
የዘውረ ደም ስርዕት በሰውነትታችን ውስጥ የሚያጓጉዘው አየር፣ ምግበ ንጥረነገር ሞለኪዩሎችን፣ ውጋጅ ቆሻሻዎችን እና የተለያዩ ተግባራትን የሚያነሳሱ ወይም የሚጨቁኑ ሆርሞኖችን ነው፤ እነዚህ ነገሮች በጣም ውስብስብ በሆነና በተሳሰረ የደም ስሮች ድር ውስጥ ይጓጓዛሉ፤ የዘውረ ደም ስርዓት ከልብ ተነስቶ ወደ ልብ በሚመለስ የደም ስሮች መዋቅር(Circuits) የተተበተበ ነው፤ ደም ከልብ ተነስቶ በደም ወሳጆች(Arteries) እና በደቂቅ ደም ስሮች(Capilla)Pages: 1