ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Skin & Body . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 04-23-17, 08:28 pm (rev. 1 by Ye Arada Lij on 04-23-17, 08:29 pm)


Karma: 90
Posts: 367/879
Since: 02-29-16

Last post: 37 days
Last view: 37 days
ጆሮ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ የአካል ክፍል ሲሆን ድምጾችን ለመስማት ያገለግላል፡፡
ጆሮ በርካታ አስገራሚ ነገሮች ያሉት ሲሆን 15ቱን እንደሚከተለው አቅርበናቸዋል፡፡
1. ጆሮ ከመጠን ያለፈ ድምፅ ሲሰማ መልዕክትን ያግዳል
ጆሮ የሚቀበለውን የድምፅ መጠን የሚመጥን ሲሆን፥ ከፍተኛ የሆነ ድምፅ በሚሰማበት ጊዜ በመጮህ ድምፁን ያግዳል፡፡
2. ጆሮ ሶስት አጥንቶች አሉት
የሰው ልጅ ጆሮ በጣም ጥቃቅን የሆኑ ሶስት አጥንቶች ያሉት ሲሆን ስታፕስ፣ ማሌውስ፣ እና ኢንከስ ይባላሉ፡፡
ስታፕስ የተባለቺው አጥንት ከሌሎች ታንሳለች፡፡
3. የሚዛን መሳት ሲያጋጥም የውስጥ ጆሮ ይጎዳል
ሰዎች ሚዛናቸውን በሚስቱበት ጊዜ ከአዕምሯቸው ጋር ግንኙነት ስለሚፈጥር ውስጣዊ የጆሮ ክፍል ጉዳት ይደርስበታል፡፡
4. ሰዎች ጉንፋን ሲይዛቸው ድምጻቸው የሚዘጋው በጆሮ ምክንያት ነው
ሰዎች ጉንፋን በማንኛው ጊዜ ሊይዛቸው ይችላል፤ በዚህ ጊዜ ታዲያ ድምጻቸው ሊዘጋ ወይም መደበኛው የአነጋገር ድምፀት ላይኖር ይችላል፡፡
ይህ የሚሆነው ደግሞ የጆሮ የመካከለኛው ክፍል በድምፅ ማስተላለፊያ ቧንቧ(Eustachian tube) አማካኝነት ከጉሮሮ ጋር ስለሚገናኝ ነው፡፡
5. ጆሮ ሶስት ክፍሎች አሉት
የውጫዊ፣ መካከል እና ውስጣዊ የጆሮ ክፍል የሚባሉ የጆሮ ክፍሎች ቢኖሩም አብዛኞቻችን ግን ውጫዊ እና ውስጣዊ የጆሮ ክፍል በሚል እንጠራለን፡፡
ውጫዊ የጆሮ ክፍል ቅርጻዊው እና በዓይን የሚታየው ሲሆን ወደ ጆሮ ታምቡር የሚገባውን ድምጽ የሚመጥን ነው፡፡
ለዚህም ያገለግለው ዘንድ የውጫዊ የጆሮ ክፍል ወጣ ገባ እና ጠመዝማዛ ቅርጽ ይዞ ተፈጥሯል፡፡
6. በመካከለኛው ጆሮ ሶስቱ የጆሮ አጥንቶች ይገኛሉ
መካከለኛው የጆሮ ክፍል ባለ እንቁላል ቅርፅ መስኮት ሲኖረው፥ ድምፅን ወደ ውስጣዊ የጆሮ ክፍል የሚያሳልፍ ቱቦ አለው፡፡
ከላይ የጠቀስናቸው ሶስቱ የጆሮ አጥንቶች የሚገኙትም በዚህ ክፍል ነው፡፡
በዚህ ክፍልም ከውጫዊ የጆሮ ክፍል የገቡ ድምጾች የጆሮ ታምቡር ንዝረት እንዲፈጥር ያደርጉታል፡፡
በዚህ ጊዜ ከሶስቱ አጥንቶች ስታፕስ የተሰኘቺው ንዝረቱን በድምጽ ማስተላለፊያ መስኮቱ ወደ ውስጥ ትልካለች፡፡
መካከለኛው የጆሮ ክፍል ድምፅ የጎላበት ሥፍራ ነው፡፡
7. የጆሮ የውስጠኛው ክፍል ድምፅ መልዕክት እንዲፈጥር የሚደረግበት ነው
በዚህ ክፍል ‘labyrinth’ የሚባል መልዕክትን ከጆሮ ወደ አንጎል የሚያስተላልፍ አካል አለ፡፡
መልዕክቱ በአግባቡ ሲተረጎምም ሰዎች መስማት ይችላሉ ማለት ነው፡፡
8. በውስጠኛው የጆሮ ክፍል የድምፅ ሞገዶች ወደ ፈሳሽነት ይቀየራሉ
በውስጣኛው የጆሮ ክፍል የሚገኙ ጥቃቅን ፀጉሮች ከድምፅ ሞገዱ ጋር በሚፈጥሩት ግንኙነት ሞገዶቹ ወደ ፈሳሽ መልዕክት አስተላላፊነት ይቀየራሉ፡፡
በዚህም አማካኝነት ጥቃቅን ፀጉሮች በፈሳሽ የድምፅ ነርቮች ተሸካሚነት ኬሚካሎችን ወደ አንጎል ይልካሉ፡፡
9. ከፍተኛ ቦታዎች ላይ ጆሮ የመስማት አቅሙ ይቀንሳል
ሰዎች ወደ ተራራማ አካባቢ ሲጓዙ ለጆሯቸው አዲስ ስሜት ይፈጠራል፤ ይኸውም በከፍታው ምክንያት ጆሮ የመስማት አቅሙ ይቀንሳል፡፡
ይህም የሚሆነው ከጆሮ ወደ ጉሮሮ ድምፅ የሚያስተላልፈው የድምፅ ቧንቧ Eustachian tube በከፍታ ስፍራዎች ባለ የከባቢ አየር ግፊት ምክንያት ድምፅን ማድረስ ባለመቻሉ ነው፡፡
10. ጆሮ በእንቅልፍ ጊዜም ሥራውን አያቋርጥም
ሰዎች እንቅልፍ በሚወስዳቸው ጊዜ ጆሮ ድምፅን መቀበል ይችላል፤ ሆኖም በእንቅልፍ ጊዜ አንጎል ድምፆች በሚላኩለት ጊዜ ያስወግዳቸዋል፡፡
11. ጆሮ ራሱን ማፅዳት ይችላል
የሰው ልጅ ጆሮ ራሱን የሚያፀዳ ሲሆን በዚህም ear wax ወይም ኩክ ይፈጥራል፡
Pages: 1