ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Natural Resources. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 04-23-17, 06:24 am


Karma: 90
Posts: 366/879
Since: 02-29-16

Last post: 65 days
Last view: 65 days
ውሃን የተመለከቱ አስገራሚ እውነታዎች
1. ጤናማ ሰው በቀን ከ11 ሊትር በላይ ውሃ መጠጣት ይችላል።
2. ከሰባ እስከ 75 በመቶ የምድራችን ክፍል በውሃ የተሸፈነ ነው።
3. በምድር ላይ የሚገኘው የውሃ መጠን 326 ሚሊየን ኪዩቢክ ማይል ነው። ምድር ስትፈጠር የነበረው የውሃ መጠን እና አሁን ላይ ያለው ውሃ እኩል ነው።
4. 97 በመቶ የሚሆነው የአለማችን ውሃ ጨዋማ አልያም ሊጠጣ የማይችል ነው። 2 በመቶው ደግሞ በበረዷማ አካባቢዎች የሚገኝ ሲሆን፥ ቀሪውን 1 በመቶ ውሃ ነው። የሰው ልጅ ለመጠጥ እና ለተለያዩ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ እያዋለው የሚገኘው።
5. 75 በመቶ የሰው ልጅ አዕምሮ በውሃ የተሞላ ነው። 70 በመቶ ገደማ ሰውነታችን ም ውሃ ነው።
6. የሰው ልጅ ያለ ምግብ ለወራት በህይወት ሊቆይ ይችላል፤ ውሃ ሳይጠጣ ግን ከሁለት ሳምንት በላይ መቆየት አይችልም።
7. ሲጠማን በሰውነታችን ውስጥ የነበረ የውሃ መጠን ከ1 በመቶ በላይ ቀንሷል።
8. ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በኋላ የምንቀንሰው ክብደት ስብ አይደለም፤ ውሃ ነው።
9. አንድ ጠርሙስ ቢራ ለማምረት 75 ሊትር ውሃ መጠቀም ግድ ይላል።
10. ሴቶች በቀን ውስጥ 200 ሚሊየን የስራ ስአቶችን ለቤተሰቦቻቸው ውሃ በመቅዳት ያሳልፋሉ።
11. ደህንነቱ ያልተጠበቀ ውሃ በየስአቱ 200 ህፃናትን ይገድላል።
12. በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ከሚከሰቱ በሽታዎች 80 ከመቶው ከውሃ ጋር የተያያዙ ናቸው።
13. የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ በጨረቃ ውሃ በበረዶ መልክ መኖሩን አረጋግጧል።
14. የአማሪካ ነዋሪ በቀን በአማካይ 378 ሊትር ውሃ ይጠቀማል፤ በአውሮፓ 189፣ በአፍሪካ ደግሞ ከ7 እስከ 20 ሊትር ውሃ እያንዳንዱ ሰው ይጠቀማል ተብሎ ይገመታል።
15. ግግር ውሃ (በረዶ) ከውሃ ይቀላል፤ ለዚያም ነው በረዶ በውሃ ላይ የሚንሳፈፈው።


Pages: 1