ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Religion. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 04-14-17, 07:16 am (rev. 2 by Ye Arada Lij on 04-14-17, 07:18 am)


Karma: 90
Posts: 357/879
Since: 02-29-16

Last post: 69 days
Last view: 69 days
ስቅለት እና ልጅነት
የ 6 ወይም 7 አመት ልጅ እያለሁ ከምንጫወታቸው ጨዋታዎች ውስጥ ትንንሽ ድንቢጥ ወፎችን ማጥመድ ነበር...
እንደ ዘንድሮ ልጅ ቪዲዮ ጌም ፣ ቦራ ፣ ኤድና ሞል ምናምን ወፍ የለም
የእጅ ማስታጠያ ወይም አነስተኛ መዘፍዘፍያ ወይም ቅርጫት በአፉ ደፍተን እስሩ ጤፍ ስንዴ ምናምን እንበትናለን ፤ በትንሽ እንጨት የተደፋውን ማስታጠብያ ገርበብ አድርገን እናስደግፈዋለን ከዛ እንጨቱን በረጅጅጅጅም ሲባጎ እናስረው እና ራቅ ብለን ተደበቀን ተቀምጠን የወፎቹን መምጣት እንጠባበቃለን...
ወፎቹ እህሉን ሊለቅሙ ሲመጡ እና ወደ ማስታጠብያው ስር ልክ ሲገቡ ገመዱን እንስበዋለን እና ማስታጠብያው ወፏ ላይ ይደፋል...
ማስታጠብያውን በጨርቅ ወይም በዶንያ ምናምን ሸፍነን ቀስ ብለን እናነሳና ወፏን እንይዛታለን...
ከዛ ያለው ደስታ በስማሞ!!!
አንድ ቀን ግን ወፏን ልክ እንዲ እይዛለሁ ብዬ ገመዱን ስስበው የማስታጠብያው ጠርዝ አንገቷን ብሎ ወፎን ገደላት!!!
ወፍ የለም!!! ምፅ ምፅ ምፅ
እና ከ7 አመቴ ጅምሮ እስከ 13/14 አመቴ ድረስ አብዛኛው ፀሎቴ እግዚአብሄር ስለዚህች ወፍ ነብስ ይቅር እንዲለኝ ነበር ፤ የእውነቴን ነው ምላችሁ እስከ ዛሬድረስ በህይወቴ እንደዚ አብዝቼ የፀለይኩበት ነገር እንዳለ ሁሉ እጠራጠራለሁ...
እና ሁሌ በየአመቱ ስቅለት በመጣ ቁጥር ቄሱ ጋር ሄጄ ንስሃ ስገባ "አባ ወፍ ገድያለሁ!!" ነበር የምለው...
ከዛ ሰው ሁሉ እርባ ሁለት ና ስድሳ አራት ምናምን ስግድ ሲባል ለእኔ ግን ቄሱ ከ 12 በላይ ስግደት ሰጥተውኝ አያውቁም ነበር...
እና አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እና ከዛ ትንሽ ከፍ ስል ደግሞ ተንከሲስ ጩጬ ሆኜ ማረባቸውን እርግቦቼን ሲበሉብኝ በ አሰቃቂ ሁኔታ የገድልኳቸው ድመቶች ብዛት በስማም ..... ምፅ
ከዛ ትንሽ ከፍ ብዬ በጉርምስናዬ ስራ ስጀምር ደግሞ ጆሮዋቸውን እየቆረጥኩ ያረድኳቸው እና ያሳረድኳቸው የ በግ ፣ ፍየል እና በሬ ብዛት በምን ይቅር እንደምባል አልገባ ብሎኝ እተወዋለው
የእውነት ግን የልጅነት ግዜ ደግ ነው ፤ የልባችን ንፅህና የየዋህነታችን ጥግ ወደር አይገኝለትም....
አሁን በጎልማሳነቴ ንስሃስ ልግባ ብልስ እንዴት አድርጌ ሃጥያቴን ዘርዝሬ ጨርሰዋለሁ?? ባስማም ብዛቱ
ከዚህስ በኃላ በኑሮ ሂደቴ ውስጥ ስንት ሃጥያት እንደምሰራ ሳስበው ገና ይደክመኛል ደግሞ ተጨማሪ ሃጥያቶችን ለመስራት ያለኝስ ዝግጁነት ቀላል መሰላችሁ እንዴ??? ሃሃሃ
አሁን ሄጄ ለቄሱ ሃጥያቴን ብናዘዝ... አንደኛ ሰአት አይበቃም መሽቶ ይነጋል በዛ ላይ ለሃጥያቴ ብዛት ስግደት ለመስጠት ቁጥር ስለማያገኙለት " ጠዋት ጠዋት እየተነሳህ እደ ፑሽአፕ እስክትሞት ድረስ ዝም ብለህ ቀሪውን እድሜህን ስገድ" የሚሉኝ ይመስለኛል
እንደኛ ሃጥያት ሳይሆን እሱ እንደ ቸርነቱ ሃጥያታችንን ይቅር ይበለን እንጂ ሌላ ምን ይባላል!!
በዓሉን ለምታከብሩ በሙሉ ከወዲሁ መልካም የስቅለት እና የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ ብለናል ኦጋኖቼ!
Pages: 1