ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Education - ትምህርት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-30-17, 09:54 pm


Karma: 100
Posts: 33/769
Since: 03-20-17

Last post: 242 days
Last view: 242 days
አንድ ሰነፍ ልጅ ገና መጀመሪያ ተማሪ ቤት የገባ እለት እንደ ደንቡ ፊደል መቁጠር ጀመረ። ከ"ሀ" እስከ "ፐ" ድረስ አንድ ጊዜ ብቻ የፊደሉን ተራ ወጣና ከሁለተኛው ላይ መምህሩ መልሶ ሲመራው "ሀ" በል ቢለው ተማሪው እንቢ አለ። ቢያባብለው ቢለምነው አሻፈረኝ እንቢ ብሎ እስከጭራሹ እያለቀሰ ሸሽቶ ከተማሪ ቤት ወጥቶ ሄደ።እያለቀሰ ሲሄድ አንድ ሰው አግኝቶት ምነው ምን አገኘህና እንዲህ ታለቅሳለህ ቢለው መምህሬ "ሀ" በል ቢለኝ እንቢ ብዬ በዚህ ተጣልተን ነው የማለቅሰው አለው። "ሀ" ለማለት ታዲያ ምን የሚያስቸግር ነገር አገኘህበት ብሎ ቢጠይቀው፣ እነዚህ መምህሮች መቼ ጣጣቸው በ"ሀ" ብቻ ያልቃል "ሀ" ስል "ሁ" በል ይሉኛል፣ "ሁ" ስል "ሂ" በል ይሉኛል፤ እንደዚህ እያሉ እስከ "ፐ" ድረስ የተፃፉትን ፊደሎች ሁሉ አንድ ባንድ ሲያስቆጥሩኝ ያለበት ድካም አንድ ጊዜ ቀምሼው አንገፈገፈኝ። ከእንግዲህ ወዲያ ይግደሉኝ እንጂ ምንም ቢሆን "ሀ" ብየ አልጀምርም ብሎ ተማሪው መለሰለትና እንደገና እያለቀሰ ወደ ቤቱ ሂደ።

ምንጭ:
ታሪክና ምሳሌ (ከበደ ሚካኤል)
Pages: 1