ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cooking & Recipes . | 2 guests
Pages: 1
Posted on 03-25-17, 05:08 am (rev. 1 by  ማማዬ on 05-04-17, 08:18 am)


Karma: 100
Posts: 78/94
Since: 08-19-16

Last post: 240 days
Last view: 47 days
የሚያስፈልጉ ነገሮች
----------------
1. ምጥን ሽሮ
2. ደቆ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
3. ደቆ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
4. ደቆ የተከተፈ ቃሪያ
5. ጎድጓዳ ሳህን
6. የእንጀራ ምጣድ ከሌላችሁ መጋገር የሚችል ወፍራም መጥበሻ
7. ጨው
8. ዘይት
9. ውሃ

አሰራሩ
-----

ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ አነስተኛ ውሃ ጨምሩ በውሃው ላይ የምትፈልጉትን መጠን ሽሮ፣ጨው፣ዘይት፣ቀይና ነጭ ሽንኩርቱን ጨምሩና በደንብ አቀላቅሉት
ውፍረቱን ውሃ ጣል ጣል እያደረጋችሁ አዙራችሁ መጋገር እንድትችሉ አድርጋችሁ አቅጥኑት፣ስታቀጥኑት እንደ አነባበሮ ሊጥ ወፍራም መሆን አለበት

በዚህ መልኩ ያዘጋጃችሁትን ብጥብጥ ሽሮ ጨዉን ቀምሳችሁ በማስተካከል አስቀምጡት በመቀጥል ለመጋገሪያ ያዘጋጃችሁትን የእንጀራ ምጣድ ወይም መጥበሻ እሳት ላይ ጣዱት
መጋሉን ወይም መስማቱን አረጋግጣችሁ የተዘጋጀውን የሽሮ ውህድ ምጣዱ ወይም መጥበሻው ላይ ጋግሩትና ክደኑት
ከ፴ ሰከንድ በኋላ ክዳኑን ከፍታችሁ በማየት የመብሰል ምልክት ካያችሁ በእንጨት ማማሰያ የስሩን ወደ ላይ በመገልበጥና በማማሰል ፍርፍር እንዲል አድርጋችሁ አማስሉት፣እሳቱ የሚበዛ መስሎ ከታያችሁ ቀንሳችሁ ረጋ ብላችሁ አማስሉት መብሰሉን ስታረጋግጡ በላዩ ላይ ቃሪያውን ነስንሳችሁ ወዲያውኑ ባዘጋጃችሁት ዕቃ ላይ አድርጉት

በዚህ መልኩ ያዘጋጃችሁትን የምጣድ ሽሮ ከተለያዩ ወጦች መሀል እንደ አይነት አብሮ ማቅረብና በእንጀራ መመገብ ይቻላል
እንዲሁም ከሌሎች አትክልቶች ጋር በማንኪያ መመገብ ይቻላል

Posted on 04-25-17, 08:19 am


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 04-25-17

Last post: 728 days
Last view: 707 days
thank you so much mamy
Posted on 05-16-17, 07:06 am


Karma: 100
Posts: 80/94
Since: 08-19-16

Last post: 240 days
Last view: 47 days
u are welcome
Pages: 1