ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cooking & Recipes . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-22-17, 09:46 pm (rev. 2 by  ማማዬ on 01-15-18, 10:38 am)


Karma: 100
Posts: 77/95
Since: 08-19-16

Last post: 140 days
Last view: 140 days
የሚያስፈልጉ ነገሮች
----------------

1. በፈላ ውሃ የተገሸረ ኩስኩስ
2. ተገርድፎ የተከተፈ የከብት ወይም የዶሮ ስጋ
3. ስጋ ከሌለ ተርሶ የተቀቀለ ወይም እሸት ቦለቄ፣አተር፣ባቄላ ወዘተ....
4. ተገርድፎ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
5. ተገርድፎ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት ወይም ዱቄት ነጭ ሽንኩርት
6. ተገርድፎ የተከተፈ ቲማቲም ከሌለ ቲማቲም ድልህ ሳይበዛ
7. ተገርድፎ የተከተፈ ካሮት
8. ተገርድፎ የተከተፈ ቃሪያ
9. የተፈጨ ወይም እርጥብ የስጋ መጥበሻ
10. የሰላጣ ቅጠል
11. ዘይት
12. ጨው
13. ዘርጋ ያለ መጥበሻ ወይም ድስት
14. የፈላ ውሃ
15. ቁንዶ በርበሬ

አሰራሩ
-----

ለምትሰሩት ኩስኩስ የውሃ ፍጆታውን በመገመት ድስታችሁ ውስጥ ውሃ፣የተፈጨ የስጋ መጥበሻ እና ቁንዶ በርበሬ ትንሽ ጨምራችሁ እሳት ላይ ጣዱት
ልትሰሩ የፈለጋችሁትን ኩስኩስ ጎድጓዳ እና ሰፋ ያለ ዕቃ ውስጥ ጨምሩት

ውሃው ሲፈላ ኩስኩሱ ላይ ገልብጣችሁ ውሃው ከኩስኩሱ ዘለል ማለቱን አረጋግጣችሁ በማማሰያ ገልበጥ ገልበጥ አድርጋችሁ ክዳኑን አስቀምጡ

የፈላው ውሃ ከበዛበት ፍርፍር በማለት ፋንታ ስለሚቦካ ሊበላሽባችሁ ይችላል ተጠንቀቁ፣ ኩስኩስ ከፈላው ውሃ ጋር ሊኖረው የሚገባው ቆይታ ከ 6-7 ደቂቃ ቢሆን ይመረጣል

በዚህ መልክ የተዘጋጀውን ኩስኩስ

1. ከተለያዩ ሳላዶች (ሰላጣ) ጋር ቀላቅሎ መመገብ ይቻላል
2. ከተለያዩ ጥራጥሬ፣አትክልትና ስጋ ጋር አብስሎና ቀላቅሎ መመገብ ይቻላል

አሁን ያዘጋጃችሁትን መጥበሻ እሳት ላይ ጥዳችሁ በጣም እንዲግል (እንዲሰማ) አድርጉት፣የተዘጋጀውን ስጋ የጋለው መጥበሻ ላይ ጨምሩና ቶሎ ቶሎ አማስሉት፣ውሃ ከወለደ ይምጠጥ፥፥ አይታችሁ ቶሎ የማይበስል ስጋ ከሆነ ውሃ ጨምሩና አብስሉት፣መብሰሉን ስታረጋግጡ ውሃውን እንዲመጥ አድርጉት
ወዲያውኑ ቲማቲም፣ነጭ ሽንኩርት እና ካሮት ጨምራችሁ አማስሉት ውሃቸው መጠጥ ሲል ዘይት ጨምሩና እንዳያር በመጠንቀቅ እሳት ቀንሳችሁ ትንሽ ጠበስ አድርጉት

ቀይ ሽንኩርቱን በመጨመር መልኩን እንዳይቀይር በመጠበቅ ቶሎ ቶሎ አማስላችሁ ሲበቃው ኩስኩሱን ጨምሩና በደንብ አቀላቅሉ ከዛም ጨዉን ቅመሱና እሳታችሁን አጥፉ
ቃሪያውን ጨምሩና አዋህዱት ወዲያውኑ በአዘጋጃችሁት መመገቢያ ዕቃ ላይ ገልብጣችሁ መመገብም ሆነ ለምግብነት ማቅረብ ትችላላችሁ

ማሳሰቢያ
-------
- ውበቱን ወይም መልኩን ለማሳመር የሰላጣ ቅጠል፣የተቀቀለ ቀይ ስር፣ብሮክሊንና የአበባ ጎመን ወዘተ... መጠቀም ትችላላችሁ
Pages: 1